ለ. በመጽሓፍ ቅዱስ መጀመሪያ ገጽ ላይ እግዚአብሔር ፈጣሪም፣ አባትም ነዉ።

Download Report

Transcript ለ. በመጽሓፍ ቅዱስ መጀመሪያ ገጽ ላይ እግዚአብሔር ፈጣሪም፣ አባትም ነዉ።

ጉባዔ ሦስት
1
SERMON-3
2
3
4
ሐ.On the abc of
the holy bible, the
LORD is creator
and father.
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
5
6
7
“በመጀመሪያ እግዚአብሔር
ሰማይንና ምድርን
ፈጠረ።”
1
ዘፍ1
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
8
†
...እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥
የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው።
አይደክምም፥ አይታክትም፥
ማስተዋሉም አይመረመርም።
ኢሳ4028
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
9
…ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን
ለብቻዬ የዘረጋሁ፣ ምድርንም ያጸናሁ
እግዚአብሔር እኔ ነኝ
ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
ኢሳ4424
†
►ከመጀመሪያዉ የነበረ እርሱ ነዉ።
ሁሉን ያዘጋጀዉም ብቻዉን ነዉ።
ከርሱ ጋር ማንም አልነበረም!
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
10
እርሱ እግዚአብሔር፡-
የማዕዘንዋን ድንጋይ አቁሞ፣
ባሕርን በመዝጊያዎች ዘግቶ፣
በላይዋ የመለኪያ ገመድ ዘርግቶ፣
መሠፈሪያዋንም ወስኖ፣
ለብቻዉ ምድርን መሥርቷል።
ኢዮ38
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
11
የዘላለም አምላክ እርሱ፡-
ለወገግታም ስፍራውን አስታዉቆ
ወደ ዳርቻው ይነዳው ዘንድ፤
የብርሃንን መኖሪያ መንገድ፣
የጨለማውንም ቦታ፣
ወደ ቤቱም የሚያደርሰውን ጐዳና
ያዉቃል። ኢዮ38
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
12
እግዚአብሔር፡ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥ ሣሩንም
እንዲያበቅል፥ ማንም በሌለባት ምድር ላይ፥
ሰውም በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብን ያዘንብ
ዘንድ፥ ለዝናብ አባት ነዉ። ለፈሳሹ ውኃ
መንዶልዶያውን አበጅቷል። መብረቆች በፊቱ
እነሆ እዚህ አለን ይሉታል፤ ለሚያንጐደጕድ
መብረቅም መንገድን አብጅቶ፣ በረዶውን በቤተ
መዛግብቱ አስገብቷል። ኢዮ38
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
13
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ፡ቃሉን ወደ ደመናት ያነሣ ዘንድ ይችላል።
የሰማይንም ሥርዓት ያውቃል።
ክዋክብትን በስማቸዉ ይጠራል፤
ለሰው ልብ ማስተዋልን አድሏል፤
ለአንበሳይቱ አደንን ያድናል፣
ለቍራ ጫጩትም መብልን ይሰጣል።
ኢዮ38
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
14
በመጀመሪያ የነበረዉ፤ ሁሉንም ያዘጋጀዉ፤
ከሆነዉም ያለርሱ አንዳች ያልሆነዉ፤ ቃል
ጸጋንና እዉነትን ተሞልቶ በእኛ ያደረዉና
ሞቶልን የተነሳዉ አምላካችንና ፈጣሪያችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ!!!
ዩሓ11-15 ፣ራእ117-18
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
15
...የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ
አይደለም እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና
እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና ስሙ
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። The
LORD of hosts is his name.
ኤር1016፣5119
16
...ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ
አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ
በሠራው መቅደስ
አይኖርም። ሥራ1724 …..ማንም ሊቀርበው
በማይችል ብርሃን ይኖራል። 1ጢሞ316 .....ስለ
ክብሩ ግን በሰማይ አለ። ማቴ69 …..በእርግጥ
ሰማይና ሰማየ ሰማያት ይይዙት ዘንድ
አይችሉም። 1ነገ827
He transcend heavens!
17
እንግዲህ አማናዊዉ
የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት
የት ነዉ?
18
...ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር
እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም
የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ
ክርስቲያን ው። 1ጢሞ316 …..ዛሬ!
Vs
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው
ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ
እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው
ይሆናል:: ራእ213 …..በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም!
19
አማናዊ ማደሪያዉ ይሆን ዘንድ
ወድዷልና፤ እግዚአብሔር ሰዉን
ለይቶ፣ አክብሮም፣ በመልኩ እንደ
ምሳሌዉ ፈጥሮታል!
20
...ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና
አመሰግንሃለሁ ሥራህ ድንቅ ነው፥
ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
መዝ13914
† በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯልና።
† በአስገራሚ የአካል ቅንብር ፈጥሮታልና።
† የድንቅ ሲስተሞች (ሰርኩላቶሪይ ዘዴ
ባለቤትም አድርጎታልና።
21
በመጽሓፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ዓረፍተ
ነገር ላይ እግዚአብሔር ፈጣሪ ነዉ።
ካልነዉ፡-
ሰዉን ለምን፣ እንዴትስ
እንደፈጠረዉ ተመለከቱ?
22
ሌላ ምሥጢር!
ግሩምና ድንቅ አድርጎ የፈጠረን
አምላካችን አባታችንም ነዉ!!!
10
ሚል2
...ለሁላችን አንድ አባት ያለን
አይደለምን? አንድ አምላክስ
የፈጠረን አይደለምን?
23
የዚህ ምሥጢሩ!
የፈጠረንና በመጀመሪያ የነበረዉ
አምላካች፣ አባታችንም መሆኑ ነዉ!
እንግዲህ
በመጽሓፍ ቅዱስ ሀሁ ላይ
እግዚአብሔር ፈጣሪም፣ አባትም ነዉ።
ያልነዉ ይህንን ነዉ!
24
በዚህም እግዚአብሔር፡ፈጣሪያችንም፣
አምላካችንም፣
አባታችንም
እንደሆነ እንገነዘባለን።
25
ሌላዉ ምሥጢር!
†
የፍጥረት ሁሉ አባትነት
የእግዚአብሔር ሲሆን፤
በምሥጢረ ሥላሴ ደግሞ
አብ አባት ነዉ።
26
...ስለዚህ ምክንያት በሰማይና
በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት
ከአብ ፊት እንበረከካለሁ። ኤፌ314-15
†
►የፍጥረት ሁሉ አባትነት የእግዚአብሔር
ሲሆን፤ በምሥጢረ ሥላሴ ደግሞ አብ አባት
ነዉ። ያልነዉ ይህንን ነዉ።
27
እንደ ሓዋሪያዉ ጳዉሎስ ትምህርት፡ኤፌ46
....ከሁሉ በላይ የሚሆን፣ በሁሉም
የሚሠራ፣ በሁሉም የሚኖር፣ አንድ
አምላክ የሁሉም አባት አለ።
በዚህም
►አባትነቱ የተለየ ፍጹምም
የመጠቀ ነዉ!!!
28
ወልዶ አባት
ከሆንዎት አባትዎ
እና
ፈጥሮም ወልዶም አባት
ከሆንዎት አባትዎ የትኛዉን
ያስበልጣሉ???
29
....አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ
እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ
ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ
እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋክፉዎች ልን? እንኪያስ
እናንተ ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት
ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት
አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?። ሉቃ1111-13
...በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር
ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም
ያውቃል። 1ዩሓ320
30
እንግዲህ፡-
አንዱ የፈጠረን አምላክ ብቸኛዉ
የምናመልከዉ አባታችንም መሆኑ
ምን ይፋይዳል?
ወይም
አምላክህ(ሽ) አባትህ(ሽ)ም መሆኑ
ምን ፈይዶሃል(-ዶሻል)?
31
አንዱ የፈጠረን አምላክ አባታችንም የመሆኑ ፋይዳ ምንድር ነዉ? ለሚለዉ፡-
የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ
የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት
ይባረክ። 2ቆሮ13
†
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ
እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል።
መዝ10313
► እግዚአብሔር አባትነቱ በርኅራኄ
የተሞላ ነዉ!!!
33
ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ
ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ
በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
1ጴጥ117
†
እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት
የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።
ምሳ312
► እግዚአብሔር አባትነቱ አድልዎ
አልባ፣ ግን ባለ ድስፕሊን ነዉ!
34
እግዚአብሔር አባትነቱ በፍጹም ፍቅር
ለይ የተተከለ ነዉ። ይህ ፈጣሪያዊና አባታዊ
ፍጹም ፍቅሩ በክብር የሚተካከለዉን አንዲያ
ልጁን እስከመስጠት ያደረሰዉ ነዉ።
†
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው
እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ
ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን
ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም
አልላከውምና። ዩሓ316-17
35
...ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥
እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር
በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር
ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ
ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን
እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው
አይደለም። 1ዩሓ48-10
... ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና
እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
ሮሜ58
36
የፈጠረን አምላክ እርሱ
እግዚአብሔር(ያህዌ ኤሎሂም) እጅግ የሚያፈቅረን
አባታችንም ነዉ። ከሚለዉ አንቀጽ ጌታን
መቀበል ወይም የእግዚአብሔር ልጅ መሆን
ማለት ምን ማለት ነዉ?
37
እግዚአብሔር እጅግ ይወደኛል፤ ልጁ
ተብዬ እንድጠራ ፍጹም ፍቅሩን የገለጠዉ፣
ክርስቶስን ስለ ኃጢአቴ በመስጠቱ ነዉ ብሎ
ማመን ነዉ።
በዚህም የእግዚአብሔር ልጅነት በጌታ ኢየሱስ
ክርስቶስ ሥራና ስም በማመን ጊዜ ከሚሆነዉ
ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ የሚገኝ ሲሆን ይህንን
ሥልጣን የሚሰጠዉም ራሱ ጌታ እንደሆነ
እንመለከታለን።
38
መጽሓፍ በ ዩሓ111-13 ፡የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ
የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም
ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
እንዳለ
አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ
ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ
አልተቀበላችሁምና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ
መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ሮሜ815-16
39
አንድም መጽሓፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡-
...ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ
ከእግዚአብሔር ተወልዶአል። 1ዩሓ51
እንዲሁ
...ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ
እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ
ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።
ዩሓ2031
እንዳለ።
40
ወደቀደመዉ ነገራችን እንመለስና፡በጉባዔ አንድ
በመጽሓፍ ቅዱስ ሀሁ ለይ እግዚአብሔር
ስሙ እግዚአብሔር ነዉ። በሚል ርዕስ ሥር
ያ የፍጥረታት ፈጣሪ ኤሎሂም በተቀረዉ
ብሉይ ኪዳን ለይ ያህዌ የተባለዉ ሲሆን፤
በአዲስ ኪዳን ደግሞ ቤዛነታችንን በደሙ
የሰራልን፤ ከስሞች ሁሉ በላይ ስም ያለዉ
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ አይተናል።
41
ወደቀደመዉ ነገራችን እንመለስና፡በጉባዔ ሁለት ደግሞ
በመጽሓፍ ቅዱስ ሀሁ ለይ እግዚአብሔር ስሙ
ኤሎሂም ነዉ። በሚል ርዕስ ያ የፍጥረታት ፈጣሪ
ኤሎሂም ልዩ ሦስትነት ያለዉ እግዚአብሔር
እንደሆነ፤ ይህንንም ጌታ በአዲስ ኪዳን
እንደገለጠዉ፤ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ
ስም የምንጠመቀዉም ወደዚህ ዘላለማዊ አንድነት
እንደሆነ፤ ለዚሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን
መግቢያዉ በር እንደሆነ አይተናል።
42
ወደቀደመዉ ነገራችን እንመለስና፡በዚህ በጉባዔ ሦስት ደግሞ
በመጽሓፍ ቅዱስ ሀሁ ለይ እግዚአብሔር
ፈጣሪም፣ አባትም ነዉ ብለን እግዚአብሔር
ፍጹም ፍቅር ያለዉ፣ የሚራራም አባታችን
እንደሆነ፤ ፍቅሩንም አንዲያ ልጁን በመስጠት
እንደገለጠዉ አዉስተን፤ የእግዚአብሔር ልጅ
መሆኛ ብቸኛዉ መንገድም፣ አምላካዊና አባታዊ
ፍቅሩን የገለጠበትን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስንና
የቤዛነት ሥራዉን ማመን እንደሆነ አይተናል።
43
የዚህ ትምህርት ዓላማ፡-
በመጽሓፍ ቅዱስ ሀሁ ለይ፡† እግዚአብሔር ስሙ እግዚአብሔር እንደሆነ፤
† ኤሎሂም ልዩ ሦስትነት ያለዉ እንደሆነ፤
† እግዚአብሔር ፈጣሪም፣ አባትም እንደሆነ
ለማመልከት፤ ይህ መሰረታዊ እምነትና
(fundamental believe) የክርስትና ሀሁ
እንደሆነ ለማሳየት ነዉ።
44
አሁን
የመጽሓፍ ቅዱስ መጀመሪያ ዓረፍተ
ነገር ለርስዎ ምንድር ነዉ?
†
አሁን
በመጽሓፍ ቅዱስ ሀሁ ለይ
እግዚአብሔር ለርስዎ ምንድር ነዉ?
45
አሁን የመጽሓፍ ቅዱስ መጀመሪያ
ዓረፍተ ነገር ለይ ኢየሱስ ክርስቶስ
ለርስዎ ምንድር ነዉ?
†
አሁን በነዚህ ሦስት ጉባዔያት
ክርስቲያን መሆን ወይም የክርስትና
ሀሁ፣ ክርስትናስ ለርስዎ ምንድር ነዉ?
46
አሁን
...ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን?
አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?
ሚል210
የሚለዉን እንዴት አዩት?
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ
እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
ሮሜ814
የሚለዉንስ?
47
በዚህም እግዚአብሔር፡የምንሰግድለት - ፈጣሪያችን፣
የምናመልከዉም - አምላካችን፣
የሚወደንም - አባታችን
እንደሆነ እንገነዘባለን።
48
.... ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ
አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፣ ነገር
ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም
በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን
በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ ደስ የሚያሰኙኝ
እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።
ኤር923-24
በዚህም ስለ እግዚአብሔር በምናዉቀዉ
ሳይሆን፤ ራሱን እግዚአብሔርን የምናዉቀዉ
ብቻ እንደሚያስደስተዉ እንመለከታለን።
መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።
49
እግዚአብሔር በመጽሓፍ ቅዱስ መጀመሪያ ገጽ
ላይ
50
ገና በፍጥረት መጀመሪያ
▼
ከበደል በሗላ
▼
እስከ አብርሃም
▼
እስከ ሙሴ
51
ዘመነ መሳፍንት
▼
እስከ ዳዊት
▼
እስከ ባቢሎን
▼
ዘሩባቤል
▼
ዕዝራ
▼
ነህምያ
52
በዘካሪያስና በሓጌ ትንቢታዊነት፤ በዘሩባቤል
መሪነት ቤተ መቅደሱን በ516 ዓ.ቅ.ክ አጠናቀቁ።
▼
በ458 ዓ.ቅ.ክ በካህኑ ዕዝራ የክህነት አገልግሎቱ
ተመሰረተ።
▼
በ445 ዓ.ቅ.ክ በነህምያ የኢየሩሳሌም ቅጥሯ
ተሰራ።
53
ነህምያ ለሚከተሉት ሕዝቡን አግባባ፡-ባለ ዕዳዎች እንዲሰረይላቸዉ ድሆችም
እንዲታሰቡ፣(ነህ512-13)
-ከአህዛብ ጋር ያለ ጋብቻ እንዲቀር
-ሰንበት እንዲከበር።(ነህ1030-31)
-አስራትና መባ በታማኝነት እንዲከፍሉ።(ነህ1037-39)
†
ከሁሉም በላይ ታላቁን ሪቫይቫል አቀጣጠለዉ።
የሕጉ መጽሓፍ ለሕዝቡ ተነበበ፣ ተብራራም፤የዳስ
በዓል ተደረገ፤ ኑዛዜ ሆነ፤ ቃል ኪዳን ተደረገ።
54
ነህምያ ወደ ቀድሞዉ ንጉስ ቤት በሄደበት
ቅጽበት ዉስጥ፡-ከባዕዳን ጋር ተጋቡ (ነህ131-3)
-አሞናዊዉ ጦቢያ ከቤተ መቅደሱ አንዱን ክፍል ያዘ
(ነህ134-5)
-ሰንበት ተሻረች።(ነህ1030-31)
-አስራትና መባ ቀረ፤ ካህናቱ ወደ ግብርናቸዉ
ተመለሱ (ነህ1010-11)
†
ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ እንደገና
ሁሉንም እንደቀድሞዉ አስተካከለዉ።
55
ከነህምያ በሗላ ግን፡-ምድራቸዉ በፋርስ ሰፊ ግዛት መካከከል
የተከለለች ትንሽ ክፍለ አገር ሆና መቅረቷ፣
-በነቢያቱ የተተነበየዉ የክብር ዘመን
መዘግየት፣
- በመዝ 68 እንደተመለከተዉ እስራኤል
መንግስቷ በአህዛብ መንግስታቶች ለይ ከፍ
ከፍ አለማለት።
ከምርኮ የተመለሰዉን ሕዝብ አላስደሰተዉም።
56
በዚህም ከምርኮ የተመለሰዉ የአይሁድ ሕዝብ፡-የእግዚአብሔርን ፍቅር አንዲጠራጠር ፤
-ፍትህ ሰጭነቱነ እንዲጠራጠር፣
-አባትነቱንም እንዲረሳ፤
-ተስፋ እንዲቆርጥ፣
ሃይማኖታዊ ሥርዓተኛ ብቻ እንዲሆን ፣
-ሕጉ ለይ ደግሞ ግዴለሽ እንዲሆን አድርጎታል።
የሚልክያስ ትንቢት በዚህ ጊዜ የተነገረ ነዉ።
እግዚአብሔር የዚህ ሁሉ ምክንያት ሕዝቡ
ራሱ እንደሆነ ለመግለጽ።
57