Transcript File

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አህዱ አምላክ
አሜን
ትምህርቱ ሃይማኖት ርትዕት


የቀናች የነላች የታወቀች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማት አስተምህሮ ይመለከታል፡፡
ወአንትሙሰ አኃዊነ ሕንፁ ርእስክሙ በሃይማኖት ቅድስት

እናንተስ ራሳችሁን በሃይማኖት አንፃችሁ ኑሩ ይሁ 1÷5
የትምህርቱ ዓላማ
 ሃይማትን ማወቅና ማሳወቅ
 አንድ ሰው ያመነበትን ያወቀውን የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለበት ለማሳየት
 ሃይማኖትን ከፍልስፍና ፍልስፍና ከሃይማኖት ለይቶ አንጠርጥሮ ያወቀ ትውልድ
ለመቅረጽ
ከዚህ ትምህርት በኃላ
ሀ. የነገረ ሃይማኖትን ትርጓሜ ይገልጣሉ
ለ. የሃይማኖትን አስፈላጊነት ያስረዳሉ፡፡
ሐ. የሃይማትንና የእምነትን አንድነትና ልዩነት ይዘረዝራሉ
መ. የሃይማትን መሠረትና አጀማመር ያብራራሉ
ሠ. የሃይማኖትን አመጣጥ ያብራራሉ
የሃይማኖት ትርጓሜና አስፈላጊነት
ሃይማኖት - አምነ-አመነ ካለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው፡፡











የማይታየውን የማይመረመረውን የፈጠረ
ያለፈውን ወደፊትም የሚሆነውን ረቂቅ ነገር እንደሆነ እንደሚሆን አምኖ መቀበል
በዚያውም ሳያወላውሉ ጸንቶ መኖር
ሁሉ በእግዚአብሔር መጋቢነት ጸንቶ ይኖራል ማለት
እግዚአብሐየር እንዴት ሊመለክ እንደሚገባው የሚነገረው
ምርምራዊ የሆነው ፈጽሞ ሊረዳ የማይቻለው እንደምሥጢረ ሥላሴ፣ ሥጋዌ
የመሳሰለው
ክርስቲያናዊ ትምህርት ነክ ቅዱስ አምልኮትንም የሚመላከተው ሁሉ
ሃይማኖት ማት ዓለም በእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ፈጣሪነት
እንደተፈጠረች ማመን
ይህንንም በእምነት ተቀብለን በእምነት እንዘገያለን
የሥራ ሁሉ መጀመሪያ የሥራ ሁሉ መፈፀሚያ ነው
በሌላ ነገር ማመን ግን ሃይማኖት ሳይሆን እምነት ይባላል፡፡
የሃይማት ምርምር



ከመፃሕፍት ከሥነ ፍጥረት
ከመምህራን
ከአእምሮ
ከአእምሮ



ሰው ሁለት ዓይነት ዕውቀት አለው
አዕምሮ ጠባይዕ
አዕምሮ መንፈሳዊ
አዕምሮ ጠባይዕ
 በጎው ከክፉ ተለይቶ የሚታወቅበት ነው፡፡
 የነፍስ ገንዘብ ናት
 ከዚህ ዕውቀት የወጡ ባለአእምሮ አይባሉም
 ይህንን ቢይዙ አእምሮ መንፈሳዊ ይሰጣል
 እግዚአብሔር በአእምሮ ጠባዕይ ላይ አዕምሮ መንፈሳዊን ክብር ይሁናቸው ብሎ
ለነበያት ሰጠ፡፡
 አዕምሮ ጠባይ የሌላቸው በእንሰሳት ይመሰላሉ፡፡
 ወደ ፈጣሪ የምትደርስ ዕውቀት ናት
 ይህ ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር እንደመጣ ይመሰክራል



ጥቂት ጥቂት እያለ የአዕምሮ ጠባዕይን ሥራ የሠራ እንደሆነ አንጽሐ ልቦና መዓርግ
የደረሰ እንደሆነ- አዕምሮ መንፈሳዊ
በእግዚአብሔር ማመን እንዲገባ ታጽናናለች ታነቃቃናለች
ወደ ንስሐ ታደርሳለች- አዕምሮ መንፈሳዊ ይሰጣል
አዕምሮ መንፈሳዊ









ረቂቅ ምሥጢርን ማወቅ ነው
መልክዐ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው
እግዚአብሔርን መፍራት ታመጣለች
እግዚአብሔርን በመፍራት ሥራ እንሠራለን
ሥራም አዕምሮ መንፈሳዊን ታመጣለች
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ስራ በርትዓተ ልብ ሆኖ የፈፀመ እንደሆነ አጽሮ
ይሠጠዋል
መጀመሪያው ጥምቀት ነው
ተምሮ ያወቁትን የማታፈርስ አይቶ ማመን ትገኛለች
ተምሮ የሚያውቁት ዕውቀት ነው፡፡
ማር ይስሐቅ
ከመጻሕፍት
 የተጻፈው ሁሉ ለእኛ ምክር እዝናት ሊሆን ተጽፏል
 መከራውን በመታገሳችን፣ መጻሕፍትም የተናገሩትም ነገር በማመናችን ተስፋችንን
እናገኝ ዘንድ ሮሜ !5÷4
 ልቦናችን መጻሕፍት በመማር በመመልከት ይለዝባል
 ሃይማኖትን ሁሉ ከመጻሕፍት ሰብስበን አንድ አደረግናት
ዮሐ አፈ.ተግሣ. !
ቅዱሳት መጻሕፍትን መንፈስ ቅዱስ ይጠብቃቸዋል
 መጻሕፍትን ባለማወቃችሁ ትስታላችሁ
 ስትቀመጥ ስትተኛ በመዓልትም በሌሊትም ቅዱሳት መጻሕፍትን ተመልከት
 ሕግህ ለሠውነቴ የተስማማ ነው መዝ )!8÷)3
 የነበያት የሐዋርያትን መጽሐፍ ወደ መመልከት ቅረብ
 መናፍቅ ተነስቶብህ የምትመልሰው አጥተህ እንዳታዝን
 ጾር ተነስቶብህ የምትመልስበት አጥተህ እንዳታዝን
 ፍጥረታትን ወደ ማወቅ ታደርሳለችና
 በዘመነ አበው፣ በዘመነ መሳፍንት በዘመነ ነገስት የተደረገውን ወደ ማወቅ ታደርሳለች

ማር ይስሐቅ አንቀፅ 1ምዕ 9
ከመምህራን




ዘለዓለም የሚኖር የእግዚአብሔር ሕጉን ጠይቃችሁ ዕወቁ ኤር 6÷!6
እኛ ግን ወንጌልን የሚያስተምር መምህራንን አብነት እናደርጋለን
ቅ.ማርያም 5÷&
ያስተማረኝ ሳይኖር በምን አውቀዋለሁ አለው ሐዋ.ሥ. 8÷#1
ወንጌልን ያስተማሯችሁ መምህሮቻችሁንም እርዱ
ዕብ !3÷7
ከሥነ ፍጥረት


-

ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ተይቶ የማያውቅ እግዚአብሔር በሥነ ፍጥረት ይታወቃል
ሮሜ 1÷@
ሃይማኖት- ሃ- ሀሎ- ያለ የነበረ
ይ- ይሄሉ- ወደፊት ይኖራል
ማ- ማዕምረ ኅቡዓት- የተሰወረውን የሚያውቅ
ኖ- ኖላዊ – እረኛ
ት- ትጉህ - የማይታክት ትጉህ
ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የተሰወረውን የሚያውቅ የማያንቀላፋ
ትጉህ እረኛ አለ ብሎ ማመን ሃይማኖት ይባላል፡፡
የሃማኖት አስፈላጊነት

ለመንፈሳዊ ሕይወት



ለሥጋዊ ሕይወት
- የጸጋ ልጅነትን
- መረጋጋትን፣ ሰላምን
- ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን - አርቆ ማሰብን
- ርስቱን መውረስን፣ ወዘተ - ከደዌ/ከሱስ መጠበቅን
- በረከት ረድኤትን
ለአገር
- መተማመን
- ትጉሕነትን
- ፍትሕን
- አክባሪነትን
- ወዘተ ያበረክታል
የሃይማትና የእምነት አንድነትና ልዩነት
 ሃይማኖት - ከላይ የተገለፀው አንድ ነው
 እምነት- የግል አስተሳሰብ
-


የግል ጥንካሬ
ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ማጥበቅ
በአንድ ነገር እድናለሁ ብሎ ማመን
እምነት - ለሃይማኖት አስፈላጊ ነው
እምነት - ብዙ አይነት ነው ሃይማኖት ግን አንዲት ናት
1
የሃይማኖት መሠረት (የዕውቀት ምንጭ)
ሥነ ፍጥረት
-
እንስሳት ይነግሩህ እንደሆነ የሠማይ ወፎችም ይነግሩህ እንደሆነ ጠይቃቸው
ትተረጉምልህ እንደሆነ ዓሳዎችም ይነግሩህ እንደሆነ ጠይቃቸው
-
ይህን ሁሉ የእግዚአብሔር ሥልጣን እንዳደረገው ማን ያውቃል ኢዮ !2÷7--------9
-
ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን
ባለመኖር አይታይ የነበረው ዓለም ካለመኖር ወደመኖር መጥቶ እንደታየ እናውቃለን፡፡
ዕብ !1÷3
-
-
2
ፈጣሪ ከፈጠረው ፍጥረት ጋር ያደረገው የቃል ለቃል ንግግር
-
ከገነት ፍሬ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካምና ክፉን ከምታሳውቀው ዛፍ አትብላ
ከእርሷ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ ዘፍ 2÷06
- እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው እንዲህም አላቸው
- ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት
ዘፍ 9÷1
- ከአብርሃም ጋር፣ ከሙሴ ጋር
ዘፍ 02÷1ዘፍ 6÷2
- እርሱም አለ ቃሌን ስሙ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር እኔ እግዚአብሔር በራዕይ እገለጥለታለሁ፡፡ ወይም
በሕልም አነጋግረዋለሁ፤ ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው፡፡
ዘኁል 02÷6—----- ---8
-
ራዕይ፣ ሕልም፣ ገሃድ ምን ማለት ነው?
3 የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት
- ሰማያትን የፈጠረና የሠራ ምድርንና በውስጧ ያለውን ያጸና፣ በእርሷ ለሚኖር ሕዝብ እስትንፋስን፣
ለሚንቀሳቀሰውም መንፈስ የሚሠጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል
ኢሳ $2÷5
- የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል
2ጢሞ 3÷!4-!7
4. በደኃራዊ ዘመን ሰው የሆነው የወልደ እግዚአብሔር አማላካዊ ቃል
- ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም
- ከወልድም በቀርና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም
ማቴ !1÷@7
----- ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ኅብረ ትንቢትና በብዙ ኅብረ አምሳል ለአባቶቻችን
ተናግሮ በዚህ ዘመን ደግሞ ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ነገረን
ዕብ 1÷1-3
- መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድስ እንኳ የለም በአባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጁ ገለጠው
እንጂ
ዮሐ 1÷!8
ምስጢረ ኩነት አምላካዊ

አካላዊ ምሥጢረ ኩነት
-
እግዚአብሔር መንፈስ ነው
ዮሐ 4÷÷@4
እንዲህ ቢሆንም፣ በሥራው ራሱን ግልጥ አድርጓል
‹‹እንወቅ፣ እናውቅ ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል እንደወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን
ሆሴ 6÷3

-
-
-
-
ቅዳሴ ማርያም ም 5ቁ qqqqq$8--%3
መለኮት አካሉ ይህን ያህላል መልኩ ይህን ይመስላል ሊሉት አይገባም
እንደ ፀሐይ እንደ ጨረቃ የሚወሰንበት ቅርጽ
እንደ ሰው ሦስት ክንድ ከስንዝር ቁመት ያለው አይደለም
ለመለኮት ወርድ ቁመት ላይ ታች ግራ ቀኝ ያለው አይደለም
በአራቱ መዓዘን የመላ ነው እንጂ
ለመለኮት የሚሮጥበት ሜዳ የሚሾልክበት ቀዳዳ የሚገባበት ዋሻ የሚመክተው ጋሻ ያለው
አይደለም /የተወሰነ ግዛት/
ለመለኮት ከታች መሠረት ከላይ ጠፈር ያለው አይደለም ማለት ከላይ ጽርሐ አርያም ከታች
በርባሮስ አይወስነውም
ለመለኮት በምድር የሆነውን ያነሳ ዘንድ ራሱን ዘንበል ማድረግ የለበትም
-
ለጴጥሮስ እንዳሳየው ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው እንጂ
ለመለኮት ደረት ግንባር
የሚታይበት በፊቱ ግንባር ደረት
-
የሚወሰንበት በኋላው ጀርባ ያለው አይደለም ባሕርዩን በባሕርዩ ይሠውራል እንጂ
-

ባሕርያዊ ምሥጢረ ኩነት

ቅዱስ ነው


1 â_éSጴጥ 1*06
ልዩ፣ንጽሕ፣ ክቡር፣ ጽኑዕ ማለት ነው
ጻድቅ ነው

‹‹አዎን ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ ፍርዶችህ እውነትና ጻድቅ ናቸው››
ዮሐ ራዕ 06*7

ፍቅር ነው



ዮሐ 3*06---07
ጥበበኛ ነው
 አቤቱ ሥራህ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ሁሉን በጥበብ አደረግህ መዝ ፻3*54
ቸር መሐሪ ይቅር ባይ ነው፡፡


‹‹ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና››
እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው፤ ከቁጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ ጻድቅ ነው፡፡
መዝ ፻2*0
ዘለዓለማዊ ነው

እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ
ኢሣ ፵4*6

ሁሉን አዋቂ ነው


በሁሉ ሙሉ የሚሆን ሁሉም ከእርሱ የተገኘ ከሁሉም በላይ ያለ የሁሉ አባት እግዚአብሔር አንድ ነው፡፡
ኤፌ 4*6
ሁሉን ቻይ ነው

ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ሉቃ.፩፣፴፯
አምላካዊ ስያሜ
-
በከሃሊነቱ ስም ‹‹ኤልሻዳይ/ አልሻዳይ›› /ከሃሊ/ በሚል ራሱን ገለጠ
በሙሴ ተጠይቆ - አህያ/ሸራህያ (ዘሀሎ/ ወይሄሉ)
- አምላክ አብርሃም፣ ይስሐቅ ያዕቆብ
- ይሆዋ/ያህዌ-(እግዚአብሔር)
- እግዚአብሔር የሚለው ስም በዓመት አንድ ጊዜ ነው በሊቀ ካህናቱ የሚጠራው
-
ሌሎችን ስሞች ከእግዚአብሔር ጋር በማጣመር በዘወትር ይጠራል
- ጌታ እግዚአብሔር
- ሕያው እግዚአብሔር
- ልዑል እግዚአብሔር አምላክ
- እግዚአብሔር አምላክ
- መጽሐፍ በአካላዊና በባሕርያዊ ስሙ ይጠራዋል



እግዚ - ገዢ፣ ጌታ(ወልድ
- አብ - አብ
- ሔር - ቸር-መንፈስ ቅዱስ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሃይማኖት በሦስቱ ሕግጋት
ዘመነ ተስፋና የዘመነ ተስፋ ኑሮ
o
ዘመነ አበው
ዘመነ ኦሪት
-
ዘመነ ድኅነት
o
ዘመነ ወንጌል
የዘመነ አበውና የዘመነ ኦሪት የእምነት አፈጻጸም መጽሐፍን በመጠቀምና ባለመጠቀም
ይለያያል እንጂ ደረጃው ተመጣጣኝ ነው፡፡ ለዚህም ዕብ 01*1- MÚ- መጨረሻ
ተመልከቱ
ዘመነ ወንጌል
o
-
-


በጌታችን የተፈፀመውን ፍጹም ድኅነት ያጠይቃል፡፡
ሃይማኖት መሠረት ናት
-
-
አሚንሰ መሠረት ይእቲ ወካልዓኒሃ ሕንጻ ወንድቅ እሙንቱ (እምነት መሠረት ናት ሌሎቹ ግን
ሕንጻና ግንብ ናቸው ዮሐ አፈ. ድር.9
መሠረት ሕንጻን እንዲሸከም እምነትም ምግባራትን ትሸከማለች
-
-
ጸሎተ ሃማኖት የሃይማኖት መለኪያ አንቀፆች አሉት
ሃይማኖት የሥራም መሠረት ናት
አምናችሁ ሥራ ካልሠራችሁ ባለመሥራታችሁ ይፈረድባችኋል፡፡
ዮሐ አፈ. ድር.9
xMñአምኖ ተጠምቆ ምግባር የማይሠራ ሃይማኖቱን ካደ
ሰው ሁሉ የሚያንጽ እንደመሆኑ ይጠንቀቅ
1 ቆሮ 3*0q
መሠረቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
ይህንን መሠረት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ ሃይማኖት ብሎታል
ሕንጻውን ምግባር ትሩፋት ብሎታል
ሃይማኖት ምግባ ትሩፋት ትሠራለች
የሚታየውን የማይታየውን ሥጋዊውን መንፈሳዊው ሥራ የምታሠራ ሃይማኖት ናት፡፡
ምግባር የሌላት ሃይማት የሞተች ናት ያዕ.፩፣፳
ከመጽሐፈ ሐዊ ስለሥራ
-
-
-
-
-
ምንም ሥራ የማይሠራ እንደስስታም እንደቀማኛ ይፈረድበታል፡፡ አባ ሎጥ
ይህች መንገድ አባቶቻችን የሠጡን መንገድ ናት በሥራ እንተጋ እንጨክን ዘንድ ዝም እንል ዘንድ
፣ስለኃጢአታችን እናለቅስ ዘንድ
ለሥራ በወጣን ጊዜ ነገር አናብዛ ትጋታችን መጠበቃችን ለሥራ ይሁን
ሁሉ ቢሟላልህ ሥራ ተጋደል
ከአባቶች አንዱ ወንዝ ዳር ተቀምጦ ከሣሩ እየነጨ እንደምንጣፍ እየሠራ ወደ ባሕሩ ይጥል ነበር ሰዎች
ሲመጡበት ተወ ቀድሞም ሥራ እንዳይፈታ እየሠራ ስለነበረ
ከመነኮሳት አንዱን ሊጠይቁ ወንድሞች ሄዱ እንዴት ትኖራላችሁ አላቸው እየጸለይን አትተኙም
አላቸው፣ አትበሉም አላቸው ሠርታችሁ ካልመጸወታችሁ ስትተኙ ማን ይጸልይላችኋል፣ ስትበሉ ማን
ይጸልይላችኋል አላቸው፡፡
አባሉክዮስ
ነፍስህን በሥራ አስጨንቃት እግዚአብሔርን መፍራት ያድርብሃል፡፡
የጌታችን የዕለተ ምጽአት ጥያቄዎች በሥራ ነው የሚመለሱት
 ብራብ አብልታችሁኛል
 ብጠማ አጠጥታችሁኛል
 ብታረዝ አልብሳችሁኛል የሚሉት
ሃይማኖትና ልዩልዩ አስተሳሰቦች
 ከዚህ ሥልጠና በኋላ




የሃይማኖትና ባህል ምንነትን ይለያሉ
ሃይማኖትና ሳይንስን ለይተው ያስረዳሉ
ሃይማኖትና ፍልስፍናን ለይተው ያስረዳሉ
የቴክኖሎጂ ጥቅምና ጉዳትን ያብራራሉ
ንዑሳን አርእስት




ሃይማኖትና ባሕል
ሃይማኖትና ሳይንስ
ሃይማኖትና ፍልስፍና
የቴክኖሎጂ ውጤቶች
ሃይማኖትና ባሕል
ባሕል - በአንድ ማኅበረሰብ /አገር/፣ መንደር፣ አካባቢ የሚገለጥ የረጅም ጊዜ የአኗኗር ዘይቤ ነው፡፡
- ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ
- ልማድ ልማድ አድርገኝ ብትል እምቢ በላት
- አንድ ጊዜ ከፈጸምካት ሁለተኛ እንድትፈጽማት ታበረታታሃለች፡፡ ማር ይስሐቅ
- ይህም በአመጋገብ፣ በአለባበስ፣ በአነጋገር በመሳሰሉት ይገለጣል
ሀ. ጠቃሚ ባሕል (ሥጋዊ)
- በአንድነት መመገብ
- በአንድነት መሥራ
- ደስታን መጋራት
ለ. ጠቃሚ ባሕል (መንፈሳዊ)
- የበዓላት አከባበር
- የዝክር/ማኅበር ተሳትፎ
- የግብረ ሰላም፣ የሰርግ ክንውን
- የመረዳዳት ባሕል ወዘተ
-
ሐ. ጎጂ ባሕል
- ያለዕድሜ ጋብቻ
- ጥንቆላና ሟርት
- የተደጋገመ ጋብቻ
- መጋደል ወዘተ…
ሃይማኖት
ባሕል
አይለወጥም
- እንደቦታውና ኅብረተሰቡ ይለዋወጣል
መገኛው እግዚአብሔር ነው
- በምክንያቶች ሊፈጠር ይችላል
መድረሻውም እግዚአብሔር ነው - ለሃይማኖት ጎጂም ጠቃሚም ሊሆን ይችላል
-
ጠቃሚ ባሕሎችን ያከብራል ያሳድጋል
-
ጎጂ ባሕሎችን ያወግዛል
* ስለዚህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖታዊ ባሕል በብዛት ጎልቶ ሲታይ ባሕላዊ ሃይማኖት ግን አልፎ
አልፎ ይታያል፡፡
-
ሃይማኖትና ሳይንስ
ሳይንስ -በአንድ ነገር ላይ ተደጋጋሚ ሙከራዎችና ጥናቶች በማካሄድ ነገሩ በሙከራዎቹ
ወቅት ከሚያሳያቸው የማይለዋወጡ ጠባዮች በመነሳት የነገሩን ምንነት
የሚገልጽ ፅንሰ ሀሳብ (Theory) አግኝቶ ዓለም አቀፋዊ እውነተኝነት ያለው
እውቀት የሚገለጽበት ነው፡፡
ጥበብ- የግል ክሂሎት ነው፡፡
ሳይንስ ለቤተክርስቲያን
-
የሥራ ቅልጥፍና /በመገናኛ ዘዴ/
የመረጃ አስተማማኝነትን /በሒሳብ፣ በቅርስ/
የቅርስ አጠባበቅ
የአስተዳደር ዘዴዎችን
ለታሪክ አመዘጋገብ
በኢኮኖሚ ዕድገት
በሃይማኖት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ
-
ከእግዚአብሔር ይልቅ ሳይንስን መተማመን
ሃይማኖታዊ ሥርዓታችን ማዳከም
ቁሳዊ አስተሳሰብን ብቻ ማጠናከር
የሥነ-ፍጥረትን ሕግ ማዛባትና መለወጥ ( ጽንስ ማቋረጥ)
የሃይማኖት ግኝቶችን ግምታዊ ማድረግ፣ ወዘተ
መጽሐፍ ቅዱስና የዘመናዊ ሳይንስ ስምምነት
- ሳይንስ ዘመኑ ዘመነ ሐቅ መሆኑን ያስረዳል፡፡
- መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን ከሚችል ኃያል አምላክ የመነጨ ስለሆነ ቢመረመር የሚገኘው ዕውቀት ነው፡፡
በዚህም ብዙ ዘመናትን አሳልፏል፡፡
ወጣት ተመራማሪ
የሃይማኖትና የሳይንስ ሰው
ዶ/ር ኼሪ ሪመር
መልስ፡- ዓለማት ከአንድ ኢምንት
ጥያቄ- ፈጣሪ ከሌላቸው ዓለማት ነገር
እየተስፋፉ
የተገኙ ናቸው
ከየት የተገኙ ይመስልሃል መልስ - ደመናዊ ቅርጽ ካላቸው
ጥያቄ- ከምን ኢምንት ነገር እየተስፋፋ
ጥርቅም ከሆኑ ነገሮች
ተገኙ
መልስ - ተፈጠሩ ይባል ይሆናል
ጥያቄ - እነዚህ ጥርቅሞች ከየት ተገኙ
መልስ - የተፈጥሮ ኃይል(በልማድ)
ጥያቄ - በማን? ወይም በምን?
ተፈጠሩ
መልስ - የተፈጥሮ … ኃይል ነው
ጥያቄ - ይህ የተፈጥሮ ኃይል
ምንድን ነው
መልስ - የማናቸውም ነገር መነሻ
ጥያቄ - ምንድን ነው
መልስ - የተፈጥሮ ኃይልን ማንም ጥያቄ - የተፈጥሮ ኃይልን ልማድን አልፈጠረውም ሁልጊዜ ነዋሪ
ማን ፈጠረ?
ነው
ስለመጽሐፍ ቅዱስ የሳይንቲስቶች ምስክርነት
-
-
-
-
-
-
አጥብቃችሁ ብትመረምሩ በሳይንስ ረገድ በእግዚአብሔር ላይ ሊኖር ስለሚገባው እምነት
ለማረጋገጥ ትገደደላችሁ፡፡ እርሱም የሃይማኖት ሁሉ መሠረቱ ነው፡፡
ሎርድ ካልቪን
በአንድ የሳይንስ ሊቅና በአንድ ክርስቲያናዊ መካከል ምንም አይነት አለመግባባት ሊኖር
አይችልም፡፡
ሮበርት በይል የቅመማ ሊቅ
ይህ የተቀደሰው መጽሐፍ ቅዱስ እያለላቸው ሰዎች ስለምን በስሕተቱ ጎዳና ይመራሉ?
ሚካኤል ፋራዲ
ከሁሉ የሚበልጠው በመካከላችን ያለው ኃይል ዛሬ አልተደረሰበትም፡፡ እንዲህም ስል በትክክለኛ
አኗኗርና በአምልኮም ስለሚገኘው መንፈሳዊ ኃይል ማለቴ ነው፡፡
ቻርለስ ፒ ስቴንመትዝ
የኤሌክትሪክ ሊቅ ጀርመናዊ
ሊኖረኝ የሚችለው እምነት እንደ ዳዊት ነው እርሱም በአምላክ ፈቃድ የገዛ ትውልዴን ማገልገል
ነው ጀምስ ክሌርክ ማክስዌል
ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሁሉ የሚበልጡ የፍልስፍና ፍልስፍና አድርገን እንገምታቸዋለን
ስር አይዛክ ኒውተን
በኪነ-ጥበብ ሊቅ እንግሊዛዊ
ሃይማኖትና ፍልስፍና
-
ፍልስፍና ማለት ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ምርምር ወዘተ ማለት ነው፡፡
ፈላስፋ ማለት የጥበብ የዕውቀት፣ የብልሃት የምርምር ሰው ነው፡፡
ፍልስፍና ለሃይማኖት የሚሠጠው ጥቅም
ሀ. ሰዎች ከተለመደው የአኗኗር ዘይቤ ወጥተው ወደተሻለ አስተሳሰብ እንዲያድጉ ማድረግ
ለ. አዳዲስና ጠቃሚ ነገሮችን ያዳብራል
ሐ. የጠያቂና የተጠያቂ አእምሮን ያጎለምሳል
መ. በሥነ-ፍጥረት ምርምር ወደ እግዚአብሔር መቅረብን ይጋብዛል፣ ያሳያል፡፡
ሠ. ከላይ የተጠቀሱትን ምርምሩ አግባባዊ መሆን አለበት፡፡
በሃይማኖት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ
 በአግባብ ካተጠቀሙበት ፍልስፍና ጉዳቱ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
-
ሥጋዊ መራቀቅን እንጂ መንፈሳዊነትን አያሳድግም
ምሳሌ የዋሕነት፣ ቅንነት፣ ትሕትና ፍቅር ያላቸውን ዋጋ አሳንሶ ማሳየት
በሥጋዊ ዕውቀትና ጥበብ ብቻ እንዲመኩ ያደርጋል
የሠዎችን ሕይወት ዘላዓለማዊነት ወደ ጊዜያዊነት ዝቅ ያደርጋል፡፡
ወደ ኑፋቄ ያመራል /ግኖስራኮች/
-
የሃይማትን ሕግና ሥርዓት ያዳክማል
ስለ እምነት መጋደል፣ ስለነፍስ መጨነቅ ዋጋ የለውም ብሎ ያምናል፡፡
በቅዱስ መጻሕፍት ጥበብ ፍልስፍና ማለት- እግዚአብሔርን መፍራት መከተል፣ ማመን፣
መታመን፣ ነው፡፡ ፍጹም ጥበብ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
ዳን 2*@
የቴክኖሎጂ ውጤቶች
ሀ. ቴክኖሎጂ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅም

-
-
ስብከተ ወንጌልን በተለያዩ መንገዶች ለማስተላለፍ
አብያተ ክርስቲያናትንና የምዕመናን ቁጥር ለመመዝገብ
ቅርብና የሩቅ ምዕመናንን በአገልግሎት ለማገናኘት
አግልግሎትን ለማቀላጠፍና ለማፋጠን
ታሪካዊ ቅርሶች አጠባበቅ
ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ለመገናኘት
ለሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት
ለርቀት ትምህርት አሰጣጥ ወዘተ
ለ. የሚያሳድረው ተጽዕኖ
-

እምነትን ያዳክማል/በቴክኖሎጂ መመካት/
ሥርዓትን ያፋልሳል/ግዴለሽነት፣ ምንአለበት/
ሕገ እግዚአብሔር እንዲጣስ ያበረታታል (ለምሳሌ ወሊድ መከላከያ ጽንስ ማስወረድ)
የመንፈሳዊና የአገልግሎት ጊዜን መሻማት ለምሳሌ (ኳስ)
ማህበራዊና መንፈሳዊ ሕይወትን ያቀዘቅዛል፡፡
ማጠቃለያ፡
-
የሰው ልጅ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ሰማያዊና ምድራዊ ሀብቱ ሃይማኖቱ ነው፡፡
ሃማኖት የሚያምነው ማንን እንደሆነ ለምን እንደሚያምን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡
ሃማትን ከፍልስፍና፣ ፍልስፍናን ከሃማኖት አበጥሮ መለየት ያስፈልጋል፡፡
ተፈላስፎ ሕገ እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም፡፡
መልካም ፍልስፍናን ሃይማኖት አያወግዝም፡፡
እያመኑ መሥራት፣ መራቀቅ፣ እተራቀቁ ማመን ይቻላል፡፡
አዕማደ ምሥጢራት
ከዚህ ሥልጠና በኃላ
ሀ. ምሥጢረ ሥላሴን
ነገረ መለኮትን ያስረዳሉ
ለ. ምስጢረ ሥጋዌን
ሐ. ምሥጢረ ጥምቀትን
ሀብታተ ቤተክርስቲያንን ይገልጣሉ
መ. ምሥጢረ ቁርባንን
ሠ. ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን - ነገረ ሕይወትን ይዘረዝራሉ
ረ. የ5ቱ አዕማደ ምሥጢር የማስተማሪያ ዘዴዎችን ለይተው ይናገራሉ
ሰ. የሃይማኖት ሥራ ሥጋዊና መንፈሳዊ መሆኑን ያብራራሉ
ንዑሳን አርእስት
1
ነገረ መለኮት
-
2
ምሥጢረ ሥላሴ
3. ነገረ ሕይወት ዘለዓለም
- ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
4. አምስቱን አዕማድ የማስተማሪያ መንገዶች
ሀብታተ ቤተክርስቲያን 5. ሃይማኖትና ሥራ
-
ምሥጢረ ሥጋዌ
-
ምሥጢረ ጥምቀት
ምሥጢረ ቁርባን
-
መቅድም
ማብራሪያ- የነገር ሁሉ መውጫ መግቢያ ማለት ነው፡፡
-
እርካብ ተረግጦ ወደ ኮረቻ
ድንክ ተረግጦ ወደ ዙፋን እንደሚወጣው
መቅድምን ተምሮ ወደዋናው ትምህርት ሲገቡ ይቀላል፡፡
አዕማድ- የአምድ ብዙ ቁጥር ነው
- ምሰሶዎች ማለት ነው
ምሥጢር - ጽርዓዊ ቃል ነው ግእዝን መስሎ ይገኛል
-
ለባለቁርጥ ዘመድና ወዳጅ የሚነገር
በወዳጆችም ዘንድ በምሥጢር ተጠብቆ የሚኖር
በእጅ የማይጨበጥ በዓይን የማይታይ በልብ የሚመረመር
ተመርምሮ የማይደረስበት በእምነት ብቻ የሚታይና የሚቀበሉት ነው
አዕማደ ምሥጢር - አዕማድ ቤተ ልቡናን በአሚን ያጸናሉ
-
አዕማድ ቤተ ልቡናን ከኑፋቄ ይጠብቃሉ
አዕማድን ያልተማረ ያላወቀ በመንጸፈ ደይን ይወድቃል በእግረ አጋንንት ይረገጣል
አዕማድን ተምሮ ማወቅ ይገባል
ሚክያሰ 4*2 - ብዙ አሕዛብ ወደ ቤተመቅደስ ይሄዳሉ … ዘጠኙን ቃላት ያስተምሩን ዘንድ በኢታምልክም
ጸንተን እንኖር ዘንድ
ከነበያት ከካህናት ትምህርት ይገኛልና፡፡
አንድም - ሕግ ጌታ ከእመቤታችን ይገኛልና
- ሕግ ወንጌል በቤተክርስቲያን ይነገራልና
- አካላዊ ቃል እርሱ በሥጋነት በደምነት ይሠጣልና
አዕማድ በሐዲስ ኪዳን በሠፊው ተነግረዋል
 1ቆሮ 04*08 - ወባሕቱ በቤተክርስቲያን እፈቅድ ኃምስተ ቃላተ እንግር
በልቡናየ
 ትርጓሜ - ነገር ግን ለምዕመናን ጥቂት ነገር ተርጉሜ እነግር ዘንድ
በልቦናዬ እወዳለሁ
 አንድም - አምስቱን አዕማድ ተርጉሜ ልናገር እወዳለሁ
በትምህርተ ኅቡአት
- በእንተ ትምህርተ ኅቡኣት ቅድመ ዘትትነገር እምጵርስ ፎራ
- ሥጋውን ደሙን ከመቀበል አስቀድሞ የምትነገር ትምህርት ይህች ናት
- ኅቡአት የተባሉት አምስቱ አዕማድ ናቸው

ምሥጢረ ሥላሴ - ሥላሴ በአካል ሦስት በባሕርይ በሕልውና አንድ ናቸው፡፡
-

አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ መሆን እንዴት ይቻላል ብሎ ልብ ሊመረምረው ቃል ሊናገረው
አይቻልምና ምሥጢር /ኅቡዕ/ ተባለ
ምሥጢረ ሥጋዌ
-
-
አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ
ረቂቁ ገዘፈ ግዙፍ ረቀቀ
ምሉዑ ተወሰነ ውሱኑ ምሉዕ ሆነ
ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ነው
አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ለኩነተ ሥጋ የመጣው ነው
የታመመው ነው ማለት አንዱን አካ ሐማሚ ኢሐማሚ ማለት
የሞተው ነው - አንዱን አካል መዋቲ /የሚሞት/
- ኢመዋቲ /የማይሞት/ ማለት
- ወተቀብረ- የተቀበረው ነው
- አንዱን አካል ከዚያ በዘባነ ኪሩብ አለ
- ከዚህ በከርሠ መቃብር አለ ማለት
- የተነሣው ነው
- አንዱን አካል ከመቃብር በአፍኣ አለ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ተነሣ ማለት
- የሞት ጻዕረኝነቱን ያሳናበተው ነው
- ከእኛ ጋር ያለን ሥጋ የሞት ጻዕረኝነቱን ያሰናበተው ነው ማለት
- ይህን ሁሉ ልብ ሊመረምረው ቃል ሊናገረው አይችልምና ምሥጢር ተባለ
-

ምሥጢረ ጥምቀት
-
-

ምሥጢረ ቁርባን
-

ቄሱ ውኃውን በብርት አድርጎ ሥርዓቱን አድርስ ቡሩክ ብሎ በባረከው ጊዜ ከጌታ በዕለተ ዓርብ
የፈሰሰውን ማየገቦ ይሆናል
ይህ የምናየው ውኃእንዴት ማየ ገቦ ይሆናል ብሎ ልብ ሊመረምረው ቃል ሊናገረው አይችልምና
ምሥጢር ተባለ
ቄሱ ኅብስቱን በጻሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ በባረከው ጊዜ የጌታን ትኩስ ሥጋና ደም ይሆናል፡፡
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ልብ ሊመረምረው ቃል ሊናገረው አይችልምና ምሥጢር ተባለ
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
-
ሰው ከፈረሰ ከበሰበሰ በኋላ እንደገና አካል ገዝቶ ይነሣል
እንዴት ሊነሣ ይችላል ብሎ ልብ አይመረምረውምና ቃል አይናገረውምና ኅቡዕ/ምሥጢር ተባለ/
- በእነዚህ ከናፍር የአምስቱን አዕማደ ምሥጢር ስልት ስልታቸውን ለይቶ መናገር አይቻልም
- ቀድሞ ረቂቅ ምሥጢር
ነበር
እነዚህን ምሥጢራት
ተምሮ ሙሉ በሙሉ ማወቅ አይቻልም
-
-

ዛሬ ለምዕመናን የጎላ የተረዳ ምሥጢር ሆኗል
በዓይነ ሥጋ ሊታይ አይደለም፡፡ በዓይነ ኅሊና ሊታሰብ ነው እንጂ
በዚህ መስቀል አምናችሁ ጸንታችሁ የምትኖሩ ሰዎች ሰውነታችሁን መርምሩ
ጀሮአችሁንም ከመስማት ከልክሉ
በአፍኣ ያለ አይናችሁንም ከማየት ከልክሉ
ዓይነ ሥጋ ካልታወረ ዕዝነ ነፍስ ካልደነቆረ አያይም አይስማምና
የኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃዱ ወንጌልን ታውቁ ዘንድ
ድኅነታችሁን የምታገኙበት አምስቱ አዕማደ ምሥጢርንም ታውቁ ዘንድ
ፈቃደ ነፍሳችሁን፣ ከጽማዌ እስከ ከዊነ እሳት ያለውን ታውቁ ዘንድ
ቅዳሴ ማርያም ምዕራፍ 6** 1
-
-
ይህን ያለፈውን ባሰብሁ ጊዜ
ልቡናዬ የልጅሽን የባሕርዩን ምሥጢር ርቀት ሊመረምር ይወዳል
ራሱን በራሱ የሚሰውርበት የልጅሽ የባሕርዩ ምሥጢር ማዕበል ሞገድነቱ ያማታዋል ያንጓልለዋል
ማለት አይመረመረውም
ዳግመኛ ልቡናዬ ልዑል ጌታን ሊመረምር ይወዳል
ካላመመርመሩ የተነሣ ይፈራል ማለት አይመረመርለትም
ከዚህ እስከ ጠፈር ያለውን መመርመር አይችልም
-
-

ይህን ያለፈውን ባሰብሁ ጊዜ በአራቱ ዓሊያን ንዑሳን መዓዛን ሊመረምር ይወዳል
የብሔ ሞትን የሌዋትንን አኗኗራቸውን ሊመረምር ይወዳል
የውቅያኖስ ጥልቅነቱን ሊያውቅ ይወዳል
የሰማዩን ምጡቅነት ሊያውቅ ይወዳል
የፈጣሪን ባሕርይ መመርመር አቅቶት ፍጡራንን ወደ መመርመር ይመለሳል፡፡
አልመረመር ብሎት ወደ ቀደመ አለዕውቀቱ ይመለሳል
አሁንም ጌትነቱን አንመርምር
የነቢያት የሐዋርያት አንደበት እንደ ጌትነቱ ለማመስገን የማይቻለው የባሕርዩን ምሥጢር ጠንቅቀን
እንናገራለን አንበል
መጽሐፈ ሲራክ 3*@1
-
ባሕርየ ሥላሴን እመረምራለሁ አትበል
ህጉን አስብ እንጂ ወደ ምሥጢሩ አያሳልፍህም
ገድል ገብተህ ባሕርየ ሥላሴን እመረምራለሁ አትበል
ብዙዎች ሰዎች ባሕርየ ሥላሴን መመርመራቸው አሳታቸው
-
የልቡናቸው ምርመራ ብዙዎች ሰዎችን አጠፋቸው እንደ አርዮስ እንደ ንስጥሮስ
-
ባሕርየ ሥላሴን መመርመር የሚወድ ሰው በእርሷ ይቀሰፋል፡፡
-
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ

በምድር ያለውን አወቀህ ተው

ከባሕር ያለውን አውቀህ ተው

በዓየር ያለውን መርምረህ ዕወቅ (በቅተህ)

የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የከዋክብትን መንገዳቸውን ሰልፍ መርምረህ ዕወቅ

ፀሐይ ጨረቃ በሕፀፅ እንዲቃረቡ በምልዓት እንዲራራቁ ዕወቅ

በሰማይ ያሉ መላእክትን እንደ ከዋክብት አድርገህ ዕወቅ

ኪሩቤልን እንደ ጨረቃ አድርገህ ከተረዳህ በኋላ

ባሕርየ ሥላሴን እንደ ፀሐይ አድርገህ ዕወቅ
ፈጽሞ መለወጥ መለዋወጥ የሌለበት ድካም ሕማም የሌለበት በባሕርይ አንድ በአካል ሦስት
የሚሆኑ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ታገኛለህ

ይህ ከአቅም በላይ እንደሆነ በዚህ አስተውል
ምሥጢረ ሥላሴ
-
ሠለሰ - ሦስት አደረገ ካለው የወጣ ጥሬ ዘር ሥላሴ ይገኛል
-


ሥላሴ ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው (በአንድም በብዙም በወንድም በሴትም ይነገራል)
የምሥጢረ ሥላሴ መሠረት ከመጽሐፍ ቅዱስ
ዮሐ 1*1- - ያ ቃል በቅድምና የነበረ ነው
- ከሥነ ፍጥረት አስቀድሞ የነበረ ነው
- አአትሪኮን፣ በርፎሪከን፣ አትርግዋን የሚባሉ ዝርዋን ቃላት አሉ፡፡ ከነዚህ ሲለይ

ስለሦስት ነገር ቃል ብሎታል
-
-
ህልውናቸውን ለመናገር- ከልብ ከእስትንፋስ ተለይቶ በአፍኣ የሚገኝ ቃል የለም
ቅድምናቸውን ለመናገር
 ልብ እስትንፋስ ቀድመውት ወደ ኋላ የሚገኝ ቃል የለም
ፈጠረበት ለማለት - አብ በቃሉ ተናግሮ ዓለምን ፈጥሯልና
ሊቃውንት ይህንን መሠረት ይዘው አምልተው አስፍተው ተናግረዋል
ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው
 ሦስትነታቸው - በስም፣ በአካል፣ በግብር
- በግብር - አብ መቸም መች ወላዲ ነው እንጂ ተወላዲ ሠራፂ አይደለም
- ወልድም ተወላዲ ይባላል እንጂ ወላዲ ሠራፂ አይባልም
- መንፈስ ቅዱስም ሠራፂ ይባላል እንጂ ወላዲ ተወላዲ አይባልም
- አብ ሠራፂ ተወላዲ ወደመሆን አይለወጥም
- ወልድም ወላዲ ሠራፂ ወደመሆን አይለወጥም
- መንፈስ ቅዱስም ወላዲ ተወላዲ ወደመሆን አይለወጥም
ሃ.አበው ዘአግናጥዮስ ም. 01 ቁ. 8
-
በአካል - አብ በአካሉ በገጹ በቅርፁ ፍጹም ነውና
-
ወልድም እንደ አብ በአካሉ በገጹ በቅርፅ ፍጹም ነውና
መንፈስ ቅዱስ እንደወልድ በአካሉ በቅርጹ ያለ ነውና
ሃ.አበው ዘአግናጥዮስ ም. @6 ቁ.3
እግዚአብሔር አካላት እንዳለው አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ
1 የጌና ስብከት ምንባብ
ስለገጽና ስለመልክ
-


ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ
ፊትህን ከእኔ አትመልስ መዝ 0*4
በሰው ፊት የካደኝን እኔም በሰማያት ባለ በአባቴ ፊት እክደዋለሁ
ስለራስ - የራስ ጠጉሩ እንደግምጃ ነጭ ነው አለ ዳን 0*4
ስለዓይን - የእግዚአብሔር ዓይኖቹ ወደ ጻድቃኑ ናቸው ጆሮዎቹም ወደ
ልመናቸው

መዝ 0*4
ስለእጆች - በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፈባቸውን የኪዳን ጽላት ሰጠው
ዘጸ #1*08



ስለአፍንጫ - እግዚአብሔር የኖኅን መሥዋዕት መዓዛ አሸተተ ዘፍ 0*@1
ስለደረት - በደረቱ ተሸከማቸው እግዚአብሔር ብቻውን መራቸው ዘዳ #2*06
ስለወገብም ስለጎኖችም - በወገቡ ጽድቅን ይታጠቃል ቅንነትም በወገቡ
ይታጠቃል ዳን 7*9

ስለእግሮች - የእግዚአብሔር እግሮች በዚህና በዚያ የቆሙበትን አለት ምታ
- ዳዊትም የእግዚአብሔር እግር በቆመበት በዚያ እንሰግዳለን አለ

ስለ አፍ - ሰማይ ሰማ ልንገርህም ምድርም የአፌን ቃል ትስማ ኢሳ 1*1
ዘዳ 07*6





በእነዚህ አካላት መብለጥ መበላለጥ ማነስ መተናነስ የለባቸውም
አብርሃም ከይስሐቅ እንዲበልጥ እንዲቀድም ይስሐቅም ከያዕቆብ እንዲበልጥ እንዲቀድም
አብ ከልጁ የሚበልጥ የሚቀድም አይደለም ወልድ ከመንፈስ ቅዱስ የሚበልጥ የሚቀድም አይደለም
ያዕቆብ ከይስሐቅ እንዲያንስ ወደኋላ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስም ከወልድ አያንስም ወደኋላ
አይሆንም ይስሐቅ ከአብርሃም እንዲያንስ ወደኋላ እንዲሆን ወልድም ከአብ ወደኋላ አይሆንም
አያንስም
አብርሃም ይስሐቅን በአባትነት ሥራ እንዲያዝዘው ይስሐቅ ያዕቆብን እንዲያዘው አብ አባት ነኝና
ብሎ ወልድን አያዘውም ወልድ ልጅ ነኝ ብሎ አልታዘዝም አይልም
ቅዳሴ ማርያም
5*%5-%6
አንድነታቸው




ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር ፊልጶስ አላወቅኸኝምን አለው
እኔን ያየ አብን አየ፡፡ እንዴትም አብን አሳየን ትላለህ፡፡ እኔ በአባቴ አባቴ በእኔ ህልው እንደሆነ
አታውቅምን
ዮሐ 04*0--@3
ከአብ የሚወጣ እኔ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ በመጣ ጊዜ ምስክሬ ነው፡፡ እናንተም ምስክሮቼ
ናችሁ፡፡
ዮሐ 05*-@
ቅዱስ ጳውሎስ ስለአብና መንፈስ ቅዱስ አንድነት በብዛት ይናገራል፡፡
ሃይማኖተ አበው ዘአግናጥዮስ
ስለአንድነታቸው ምዕ 01*6
-
-
በአምላክነት አንድ ናቸው
በፈቃድ አንድ ናቸው
በኃይል አንድ ናቸው
በመንግስት አንድ ናቸው
በመሰገድ አንድ ናቸው
በመመስገን አንድ ናቸው
በምክር አንድ ናቸው
በሥልጣን አንድ ናቸው
በክብር አንድ ናቸው
በሁሉ አድሮ ሁሉን በማክበር አንድ ናቸው
ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ * 4*6
 በአገዛዝ - መገዛት መታዘዝ የላቸውም አንዱ አንዱን አይገዛውም አያዘውም
- በጌትነት በክብር አንዱ ከአንዱ አይበልጥም

በቅድምና - አብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ዓይን ከፍቶ
የሚገጥሙትን ገጥሞ የሚከፍቱትን ያህል አልነበረም
- ወልድም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በዘመን አልነበረም
ሃይ.አበው ዘኪራኮስ ምዕ (1*3
 በሥራ ፈቃድ አንድ ናቸው፡-
አብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በብቻው ሥራውን የሚሠራ አይደለም
ወልድም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የሚሠራ አይደለም
መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ ሥራውን የሚሠራ አይደለም አብ የሚሠራውን ወልድ
መንፈስ ቅዱስ ይሠሩታል እንጂ
ምሥጢረ ሥላሴ በቅዱሳት መጻሕፍት
በብሉይ ኪዳን
-
እግዚአብሔር የአባቶችህ የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ ፈጣሪ እኔ ነኝ አለው
ዘጸ 3*6
አምላክ ብሎ ቃሉ አለመአወጡ የአንድነት ሦስት ጊዜ መነገሩ የሦስትነት
የእግዚአብሔር ይቅርታው ምድርን መላ ማለት ምድርን ፈጠረ - አብ
-
ለይኩን ባለው ቃሉም ሰባቱ ሰማያት ተፈጠሩ አንድም ጸንተው ይኖራሉ - ወልድ
-
ከረቂቅ ሥልጣኑም የተነሣ ሰማይ ከነግሡ ምድር ከነልብሱ ተፈጠሩ - መንፈስ ቅዱስ
መዝ #2*5-6
እግዚአብሔር አብ ገናና ነው እግዚአብሔር ወልድም ገናና ነው ጥበቡ እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስም ሀብቱ ፍጹም ነው
መዝ )$6*5
-
-
-

አንዱም ከአንዱ ጋራ ጩኸው ያመሰግናሉ



አንድም ቅዱስ/ 3 ጊዜ/ አንድነቱን



ቅዱስ ብለው ሦስትነቱን
እግዚአብሔር ብለው አንድነቱን
እግዚአብሔር ብለው ሦስትነቱን
እግዚአብሔር የሦስቱ ስምነውና
አንድም ቅዱስ /3 ጊዜ/ ያለው የሦስትነቱን

ቃሉ አለመለወጡ የአንድነት

አንድም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያለው
የአንድነት የሦስትነት ይሆናል
 እየራሳቸው ልብ፣ እየራሳቸው ቃል
እየራሳቸው እስትንፋስ ቢኖራቸው
ቅዱሳን ቅዱሳን ባሉ ነበርና ኢሳ 6*3

በሐዲስ ኪዳን
በመንፈስ ቅዱስ ፍጹማን ሁኑ
መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን
እግዚአብሔር አብንም በማመስገን (መንፈስቅዱስ ወልድ አብ አለ) ለማስተካከል ዕሪናቸውን ለመናገር
2 ጴጥ 3*08
ስታጠምቋቸውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው
ማቴ @8*!9
-
-
-
-
•
•
ሕዝቡ ሁሉ ከተጠመቁ በኃላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ፡፡ ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም
በአካለ መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል
ድምጽም ከሰማይ መጣ፡፡
ሉቃ 3*@1-@2
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋው የእግዚአብሔርም ፍቅሩ የመንፈስ ቅዱስም አንድነቱ በእናንተ
ጸንቶ ይኑር አሜን፡፡
2 ቆሮ 03*04
-ነገር ግን በስሜ ብታምኑ አብ የሚልክላችሁ ጰራቅሊጦስ ሁሉን ይገልጽላችኋል እኔ የነገርኳችሁን
ሁሉ ያሳስባችኋል፡፡
ዮሐ !4*@6
ምስጢረ ሥላሴ በምሳሌ
1
ሰው - በቃሉ - ወልድ





በትንፋሹ - መንፈስ ቅዱስ
በልቡ - አብ
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ግን ፍጹም መልክ ገጽ ፍጽም አካል አላቸው፡፡ ዝርዋን አይደሉም
ከላይ የተጠቀሰው ምሳሌ በከዊን መገናዘብ ነው፡፡
ከዊን ማለት - እንዲህ ቢሆን እንዲህ መሆን ነው ተብሎ የሚነገር ነው፡፡
ይህ ምሳሌ እንደሚያንስ _አብ እንደሰው ወልድ እንደቃሉ መንፈስ ቅዱስም እንደ አንደበቱ
እስትንፋስ ነው የሚል ቢኖር የተለየ ይሁን



አብ እንደ ፀሐይ ወልድ እንደ ብርሃን መንፈስ ቅዱስም እንደ ሙቀቱ ናቸው፡፡ የሚል ቢኖር
የተለየ ይሁን
ፀሐይ ያለብርሃኑ ሞገስ የለውም የፀሐይ ልብሱ ብርሃን ነው ወልድን በልብስ እንጂ በእውነተኛ
ፀሐይ አልመሰሉትምና
መንፈስ ቅዱስም ሙቀት ብቻ ብርሃን የሌለው ከሆነ ሲኦል ሆነ ማለት ነውና፡፡
መጽሐፈ ምሥጢር የፋሲካ ዓርብ ምንባብ
2 . እሳት - በፍሕሙ − አብ
- በነበልባሉ − ወልድ
-በሙቀቱ − መንፈስ ቅዱስ
3 . ባሕር - ስፋት - አብ

- ርጥበት - ወልድ
- ሁከት - መንፈስ ቅዱስ
እንዲህ ስለሆነ ሦስት ባሕር አትባልም አንድ ባሕር ትባላላች እንጂ
4 . ጉንደ ወይን - ቅጠሉ - ወልድ
ፍሬው - መንፈስ ቅዱስ
ግንዱ - አብ
5 . ጎሕ - አካሉ - አብ
ርቀቱ - መንፈስ ቅዱስ
ብርሃኑ - ወልድ
6 . ቅቤ - አካሉ - አብ
- ግዘፉ - ወልድ
- ርቀቱ - መንፈስ ቅዱስ
ቅዳሴማርያም 5*&1-&5

እነዚህ ምሳሌዎች እጅግ ያነሱ ሲሆን ከነዚህ በታች ወርዶ በሌላ መመሰል
አይመችም፡፡
ምሥጢረ - ሥጋዌ






ተሠገወ - ሰው ሆነ፣ ሥጋ ለበሰ፣ ጐላ ገዘፈ
ሥግው - ሥጋ የሆነ ሥጋ የለበሰ ሥጋማ ግዙፍ
ሥጋዌ - ሥጋነት፣ ሥግና ሥጋ መሆን የሥጋ ባህሪይ መወፈር መግዘፍ
ትሥጉት - ሥጋነት፣ ሰውነት፣ ሰው መሆን ሥጋ መልበስ፣
ምሥጢረ - ሥጋዌ - የሥጋነት የሥግና ሥጋ የመሆን የሥጋን ባሕርይ ገንዘብ የማድረግ የመወፈር
የመግዘፍ ምሥጢር ማለት ነው፡፡
ስለ ምሥጢርነቱ መቅድሙን ይመልከቱ፣
ክብረ- አዳም፣
፩ እግዚአብሔር ዓርብ በነግህ በእኛ አምሳል በእኛ አርአያ ሰውን እንፍጠር አለ
ዘፍ-፩÷፳፮
፪ ሁሉን ስለአዳም በመፍጠሩ ( አክሊማሮስ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን
ግብረ
ህማማት የሰኞ የነግህ ምንባብ )
፫ ሌሎቹን ለይኩን ባለው ቃሉ ሲፈጥር አዳምን ግን በእጁ ስላበጃጀው
ማር. ጥስሐቅ
፬ ሰውን አቃንቶ በመፍጠሩ (አክሲማሮስ የዓርብ ምንባብ )
፭ አዳም ወደ ገነት ሲገባ በተደረገለት ክብር
/ኩፋ ፬÷፱-፲/
ድቀተ አዳም፣

አዳም እከብር ባይ ልቦና ስላደረበት ወደቀ
ሉቃ ፲፪÷፲፮

ዲያብሎስ በዚህ ቀደዳ ተጠቅሞ ዕፀ-በለስን እንዲበላ አደረገው፣
መቅድመ ወንጌል ፫ኛ ጉባኤ
በዚህ ስህተት አዳም አራት በደሎችን በደለ
፩ ጾምን ሻረ ፪ ወደ እግዚአብሔር መለመንን ተወ
ንጽሐ ሥጋን አፈረሰ

፫ የእጅ ሥራን ተወ
መጽሐፈ ሐዊ ባህል ፵፬
አምላክ ለምን ሰው ሆነ፣
- እግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም ይመጣ ዘንድ፣
- ከንጽሕት ድንግል ሥጋን ይዋሃድ ዘንድ ምን አተጋው
- ጨርቅ ይለብስ ዘንድ በጐል ይጣል ዘንድ፣
- የእመቤታችንን ጡት ጠብቶ ያድግ ዘንድ፣
-
በዮርዳኖስ ይጠመቅ ዘንድ---- ምን አተጋው ብትል እኛን ለማዳን ነው፣
ሃ.አበው ዘእለእስክንድሮስ
፬

ይህንንም ወዶ በፈቃዱ አድርጐታል፣





ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ወደ ፈጠራቸው ፍጥረታት ተመለከተ፣
ወደ ጽኑ አገዛዙ መሄዳቸውን አይቶ፣
በይቅርታው በቸርነቱ ብዛት አዘነላቸው፣
ስለሁለት ነገር አዳምን ሊያድነው ወደደ፣
፩ አላበጀሁም ብሎ አዳም ስለተጸጸተ
፪ አዳም ፈጽሞ መዋረድን ስለተዋረደ
መቅድመ .ወ አራተኛ ጉባኤ
በራሱ ፈቃድ፣ ባባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ሆኖ አዳነን፣
ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ








ወደ ጴጥሮስ ተመልሶ ሰይጣን ከኋላዬ ወግድ አለው፣
ማቴ ፲፮÷፳፮
ጴጥሮስ ሰይፍህን ወደሰገባው መልስ አባቴ የሰጠኝን ጽዋ ሳልጠጣ
ዩሐ ፲፰÷፲፮
በራሱ ፈቃድ አሰቃዩት
በራሱ ፈቃድ ገደሉት
በራሱ ፈቃድ በቅንዋተ መስቀል ሰቀሉት፣
በራሱ ፈቃድ በሥጋ የሞትን ጽዋ ተቀበለ
በራሱ ፈቃድ ከሐሞት ጋር መራራ የተጨመረበትን አጠጡት
በራሱ ፈቃድ ነፍሱን ከአባቱ ዘንድ አማጸነ፣
አልተውም፣





በራሱ ፈቃድ በወታደር ጦር ተወጋ
በራሱ ፈቃድ ከጐኑ ደምና ውሃ ፈሰሰ
በራሱ ፈቃድ በመቃብር ውስጥ ሶስት መዓልትና ሶስት ሌሊት ያለመንቀሳቀስ አደረ
በራሱ ፈቃድ ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሶ በመለኮቱ ኃይል ተነሳ
መጽሐፈ ምሥጢር በዓርብ የነግህ ምንባብ፣
አምላክ እንዴት ሰው ሆነ



ጥንቱን የማይመሳሰሉ ባህሪያት በማይለይ ተዋቅዶ አንድ ሆነው አንድ ክርስቶስ አንድ
እግዚአብሔር አንድ ወልድ እንደሆነ እናምናለን ይኸውም በመለኮትና በትስብእት
ተዋህዶ ነው፡፡
ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ ፲፪
ሥጋ ሁሉን የሚያድን የቃል ገንዘብ ሆኖ ከሞት ከሙስና ድኖ ይኖር ዘንድ ሥጋን
እንደ ተዋሃደ፣
በዚህ አምሳል ነፍስም ኃጢአት የሌለበት የቃል ገንዘብ ሆና ከሞት ከሙስና ድና ትኖር
ዘንድ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምናለን፡፡
ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ
፲፫

‹‹እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ቃል››
መለኮት ገንዘብነቱን ሳይለቅ የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ እናዳደረገ ሥጋም ገንዘብነቱን
ሳይለቅ የመለኮት ገንዘብ ሆነ በፍጹም መጣባበቅ፣

ክርስቶስን ነፍስ አልነሣም የሚሉት ከመከራ ያገቡታል ከማዳን ያወጡታል፣

ምትሐት የሚሉት ከመከራም ከማዳንም ያወጡታል፣

ኩለንታሁኬ ለቃል ወኩላንታሁ ለትስብእት ከመ ተደመረ ነእምን››
 ትርጉም፡- ፍጹም የቃል ባህርይና ፍጹም የሥጋ ባህሪይ እንደተዋሀዱ እናምናለን፡፡

አማናዊ ለሚሆን ለሥጋችን ሥጋውን ክሶ ለሁሉ ነፍስ ቤዛ ነፍሱን ክሶ ሕያዋንን
ሙታንን ይገዛ ዘንድ ሰውነቱን ለሕማም ለሞት አሳልፎ ሰጠ፣
በዓፀደ ሥጋ ላሉ በአካለ ሥጋ እንዳስተማረ በዓፀደ ነፍስም ላሉ በተዋህዶ ገንዘብ
ባደረጋት በአካለ ነፍስ አስተማረ፣
በዓለመ ሥጋ ላሉ ሠላሳ ሶስት ዓመት እንዳስተማረ፣ በዓለመ ነፍስም ላሉ ሠላሳ ሶስት
ሰዓት አስተማረ፣



ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ ፲፭
የአባ ጊዩርጊስ ዘጋሰጫ መጽሐፈምሥጢር የኖላዊ ንባብ፣





ያለ እግዚአብሔር ብቻ ኃጢአትን ይቅር ማለት ለማን ይቻለዋል?
ሥጋን መዋሀዱ ከሰው ወገን ባይሆን ኖሮ የኢያኢሮስን ልጅ ልጄ ብሎ ባልጠራ ነበር፣
በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን ኖሮ ከሞተች በኋላ ለህይወት ባላስነሳት ነበር፣
ሥጋን መዋሀዱ ከሰው ወገን ባይሆን ምራቁን ከአፈር ላይ ባላደረገ ነበር
በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን ምራቁን በመቀባት ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው ዓይን ባላበራ
ነበር

ሥጋን መዋሀዱ ከሰው ወገን ባይሆን ማዕበል ሲነሳ በጀልባ ውስጥ ባልተኛ ነበር፣

በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን ባህሩን ነፋሳትን በመገሰጽ ጸጥ ባላሰኘ ነበር፡፡
ሥጋን መዋሐዱ ከሰው ወገን ባይሆን መንገድ በመሄድ ባለደከመ ነበር፣
በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን መሄድ የተሳናቸውን ባላዳናቸው እንደጐበዝ ተራማጅ ባላደረጋቸው ነበር፣
ሰው መሆኑ ከሰው ወገን ባይሆን ኖሮ ባልተራበ፣
በመለኮቱ ፈጣሪ ባይሆን አምሰት ሺ ርኁባንን በአምስት ኅብስትና በሁለት ዓሣ ወራት መቶ
ርኁባንን በሰባት እንጀራና በጥቂት ዓሣ ባላጠገበ ነበር፣




የክርስቶስ ክብር ከራሱ እንጂ ከሌላ የተገኘ አይደለም፡፡





በመንፈስ ቅዱስ አዋሀጅነት ከአብ በተገኘ በባሕርይ ክብር ከብሯልና ስለዚህ ክርስቶስ ተባለ፡፡ ክብሩም አካለ ቃል
ነው፡፡
ሥጋን ያልተዋሀደ ዕሩቅ ቃልስ ከሆነ ከበረ መባልን አይሻም
በባሕርይ ክብሩም ላይ ክብር አልተጨመረለትም
ያለ ሀሰት በውነት የሚበልጥ ቃል የሚያንሰውን ሥጋ ያከብረዋል፡፡
 ለሰው ባሕርይ በነፍስ በሥጋ ከበረ መባል ይገባዋልና (ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ ፳፱)
ከአብ በተገኘ በባሕርይ ክብሩ ከብሮ ክርስቶስ የተባለ እርሱ ቀዳማዊ ነው፡፡
ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ ፳፬

ሥላሴ በከዊን ከመገናዘብ በቀር አንዱ አካል በአንዱ አካል አያድርም አንዱም ለአንዱ ክብር አይሆንም በክብር
ዕሩያን ናቸውና፡፡

የተዋህዶ ምሳሌዎች፡፩ ዕንቆ ባህሪይ በዘር በሩካቤ የሚገኝ አይደለም ከውሃና ከመብረቅ ተዋህዶ ነው እንጂ ፣
ሃ.አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም
፪ የፀሐይ ብርሃንና ግንድ ፀሐይ በምሳሩና በዘፍ ላይ ወድቆባቸው ሳለ ክርክራት ፍልቃት ሊወጣበት አይቻለውም ክርስቶስም
በለበሰው ሥጋ ታመመ እንጂ በባሕርይ መለኮቱ ህማም የሚያገኘው ነው፡፡ ሃ.አበው ዘሰላባስትርዮስ
፫ ብረት ከእሳት ጋር በተዋሀደ ጊዜ ሃ.አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ
፬ የነፍስና የሥጋ ተዋህዶ
ሃ.አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ

የክርስቶስን የማዳን ጉዞ ተወያዩበት
የክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጣት በትንቢተ ነቢያት፣
፩ ሲራ ፳፬÷፩-፲፫

አራቱንም መዓዘነ ዓለም ብቻዬን ዞርሁ /በምላት/፡፡…… በየብስም ሁሉ ፴፫ ዓመት ከ፫ ወር
ኖርሁ በአህዛብም ሁሉ በሕዝብም ሁሉ ዘንድ ከአምስት ሺ ከአምስት መቶ ዘመን አስቀድሞ
የባሕርይን ተዋህዶ የጸጋንም ተዋህዶ ገንዘብ አላደረግሁም፡፡
፪ ትንቢተ ዳንኤል ፯፤፲፫

መጻሕፍት ተገለጡ አለ ይህም ስለክርስቶስ ሰው መሆንና
የነቢያት ቃል ነው፡፡
መምጣት የተናገሩት
፫ እነሆ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ትወልዳለች ኢሳ ፯፤፲፬
-
-
ህፃን ወልደ እግዚአብሔር ክፉውን ከበጐ ለይቶ በጐውን ይወዳል
ኢሳ
፯፤፲፭
ለጌታ ስልጣን የባሕርይ ነው፣ አንድም መስቀል በትከሻው ላይ ሆነ አንድም ምዕመናንን
በነፍስ አጸናቸው፡፡ ጌታ ምክሩ ሥጋዌ የተደነቀለት ይባላል መምህረ ወንጌል ይባላል እኔ
ለሐዋርያት ፍቅር አንድነትን አመጣለሁ፡፡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በፊት
ተአምራት ይደረጋል ኢሳ ፱÷፮-፯
፬ ጽኑ ክቡር የሚሆን ከነገደ ይሁዳ ከተወለደች ከእመቤታችን ይወለዳል፡፡
፫÷፫
ዕንባ
፭ አንቺም ቤተልሔም ኋላ ትበዥ ዘንድ ዛሬ አንሰሻል እስራኤል ዘነፍስን የሚጠብቅ ጌታ
ባንቺ ይወለዳልና፣
ሚክ ፭÷፪
፮ የኦሪት የወንጌል ልጅ ደስ ይበልሽ የባሕሪይ አምላክ ክርስቶስ ይመጣልና ዓለሙን
የሚያድን ኃዳጌ በቃል ክርስቶስ ይመጣልና
ዘካ ፱÷፱
፯ እኔስ በማህጸነ ማርያም ነግሻለሁ፣
መዝ ፪÷፮
፰ ከህፃናት አንደበት ምስጋናን ተቀበለ
መዝ ፲÷፪
፱ እጄን እግሬን ቸነክሩኝ
መዝ ፳፩÷፲፮
ኦሪት ወነቢያት ሰበኩ በክርስቶስ –ኦሪትና ነቢያት ክርስቶስን አስተማሩ፣
ምሥጢረ ጥምቀት፣


ተጠምቀ - ተጠመቀ፣ ተነከረ፣ ታጠበ፣ ተጣጠበ፣ በገዛ እጁ ወይም በሰው
እጅ
ጥምቀት - በቁሙ፣ ማጥመቅ፣ አጠማመቅ፣ ጠመቃ፣
የማጥመቅና የመጠመቅ ሥራ ፣ኅጽበት
( በጥሩ ውሃ የሚፈጸም ) ፣ የበዓል ስም

ምሥጢረ ጥምቀት - የመነከር፣ የመታጠብ፣ የመተጣጠብ ሥርየት ለማግኘት የሚደረግ ምሥጢር
ነው፡፡
 ሌሎቹን ምሥጢራተ ቤ/ክርስቲያን ለመሳተፍ በር ነው፡፡
- በክርስቶስ ተመሰረተ፣
- የክርስትና መብት የሚገኘው በነገድ፣ በዘር ፣ በኃይል ሳይሆን በጥምቀት ነው፡፡
- ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ካልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማየት
የሚችል የለም፡፡ ዮሐ ፫÷፫-፯
የጥምቀት መስራች ክርስቶስ ነው፣
-
-
ለጌታ ሰላሳ ሲሞላው ለዮሐንስ መንፈቅ ሲያልፈው ያንጊዜ ጌታ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ፣
ማቴ ፫÷፲፫
ጌታ ወደ ባሪያው የሄደው ለትህትና ለአብነት ነው፡፡

በዮርዳኖስ የተጠመቀው፣
ትንቢቱ ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ
ትንቢት፡
ኤርትራ በሙሴ በአሮን አድሮ ሥራውን ሲሰራ አይታ ሸሽች አንድም ዮርዳኖስ ጌታን አይታ ሸሸች
መዝ ፻፲፫÷፫
- ማየተ ኤርትራ አዩህ ዓይተውህም ፈሩ አንድም ማያተ ዮርዳኖስ ዓዩህ ዓይተውም ፈሩ፣
መዝ ፸፯÷፲፮
ምሳሌ፡ዮርዳኖስ
አዳም
-
-
ዮር
ዳኖስ
ዮርዳኖስ
አህዛብ
ህዝብ
በክርስቶስ በጥምቀት
፪ አብርሃምን መልከ ጼዴቅ ጽዋዐ አኮቴት ኅብሰተ በረከት ይዞ ተቀበለው
ዘፍ ፲፬÷፲፬
-

3
ዮርዳኖስ - የጥምቀት
አብርሃም - የጥሙቃን
መልከ ጸዴቅ - የቀሳውስት
ኅብስተ በረከት ጽዋዐ አኮቴት – የሥጋውና የደሙ

አንድም፡-
እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል፡፡ ምዕመናንም አምነው ተጠምቀው ገነት
መንግስተ ሰማያት ገብተዋል፡፡
3. ከኤልሳዕ ደቀ መዛሙርት አንዱ ዕንጨት ሲቆርጥ ምሳሩ ከዛቢያው ወልቆ ከባሕር ገባበት፣ አሳየኝ አለው
ቅርፍተ ዕፅ ቀርፎ አመሳቅሎ ቢመታው መዝቀጥ የማይችለው ቅርፍተ ዕፅ ዘቅጦ መዝቀጥ
የሚገባውን ብረት ይዞት ወጥቷል
 ምሳሌው ፡- ሞት የማይገባው መለኮት በለበሰው ሥጋ ሞቶ ሞት የሚገባው አዳምን ማዳኑ ነው፡፡
መጠመቁም ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን ለማድረግ ነው፡፡
-
4. ዮርዳኖስ
-
በበጋ የማይጎድል በክረምት የማይተርፍ ማዕከላዊ ውሃ ነው፡፡
የጌታም ጥምቀት እኛን ከመጥቀም በላይ እርሱን ከመጥቀም በታች ነው
ዮርዳኖስ ሌሎቹን ወንዞች ያበረታል የጌታም ጥምቀት ለእኛ ኃይል ጽንዕ ይሆናል፡፡
5 ኢዮብ ንዕማን - የአዳም ከነሕፃናቱ ፣ ደዌ−የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ ፣ ዮርዳኖስ– የጥምቀት፡፡
ኢዮብ፣ ንዕማን ጌታ የተጠመቁበት ወደቡ አንድ ነው፡፡
ምሥጢሩ ግን
1 Myየዕዳ ደብዳቤያችንን ከባላጋራችን ያጠፋ ዘንድ ነው ቈላስዩስ 2*4 ኤፌØ 2*05
ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ትትፌሣሕ

-
ጥምቀቱን በውኃ የደረገው
ትንቢቱ ምሳሌው ሊፈፀም ነው
ትንቢት 1… በማየ ምንዛኅ በማየገቦ እረጫችኋለሁ አፍአዊ ውሳጣዊ ንጽሕ ትነጻላችሁ
ከኃጢአት ከጣዖት ከፍዳ ከመርገም አነጻችኋለሁ፡፡
ሕዝ #6*@5
2 œ- ከውኃ የተጠሙ ሰዎች ሁሉ ወደ ውኃ ይሂዱ
- ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ያለዋጋ ልጅነቱን ይቀበሉ ዘንድ ይሂዱ ኢሳ %5*1
3 - ልጅነትን የሚፈልጉ %)5) ዘመን አንደበታቸው በፅምዐ ነፍስ የተያዘ
ልጅነትን ክብርን ያገኛሉ፡፡
ኢሳ $1*07
4 -- በተራራው ፈሳሹን ውኃ አፈልቅላቸዋለሁ አንድም ከጳጳሳት ክብርን
እሰጣቸዋለሁ፡፡
ኢሳ $1*08
Mምሳሌ፡- አክሲማሮስ ዘሐሙስን ተመልከት
- ውኃ ለሁሉ ይገኛል ጥምቀትም መሠራቱ ለሁሉ ነውና
- ውኃ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይፈሳል ጥምቀትም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ
ይደረጋልና፡፡
-
ምዕመናን
ልጅነትን
- ውኃ ያነጻል ጥምቀትም ያነጻልና
- ውኃ ለወሰደው ፍለጋ የለውም በጥምቀትም የተሰረየ ኃጢአት በፍዳ አይመረመርምና
- ውኃ መልክ ያሳያል፣ መልክ ያለመልማል ጥምቀትም መልክአ ነፍስን ያለመልማልና
-
-
-
-
በውኃ የታጠበ ልብስ ኃይል ጽንዕ ግዘፍ እየነሣ ይሄዳል ምዕመናንም ተጠምቀው
ገድል ትሩፋት እያከሉ ይሄዳሉና
ሥጋዊ ተፍኅሮ የነሲፓራ የነርብቃ በውኃ ተደርጓል መንፈሳዊም ተፍኅሮ
በጥምቀት ነውና
ሸክላ ሰሪ የነቃባት እንደሆነ እንደገና ከሳክስ በውኃ ታድሳዋለች
ተሐድሶም በጥምቀት ነውና
ቀድሞ በውኃ ሰብአ ትካትን ሰብአ ግብጽን አጥፋቷል ውኃ ለጥፋት እንጂ ለልማት
አይሆንም ብለው ነበርና ለልማትም እንደሆነ ለማሳየት
ምዕመናን በጥምቀት ማግኘት ኃይል ድል ይነሣሉና
-
የማይታይ መንፈስ ቅዱስ በሚታይ አገልግሎት በሰው ያድራል
- ኒቆዲሞስ ጌታን ጠይቆ ተረድቷል፡፡
ዮሐ 3÷3
-
መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በእሳት አምሳል ራሱን ገልጧል
የአባ ጊዮርጊስ መጽሐፈ ምሥጢር
ሦስተኛ የጥምቀት ምንባብ
መንፈስ ቅዱስ ዘወትር በወፍ ብቻ የሚመሰል ቢሆን ኖሮ በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ በእሳት
አምሳል ለምን ወረደ?
- በርግብ አምሳል የታየው ርግብ የዋህ ናት በግም ከሁሉ እንስሳ የዋህ ነው- ጌታ
- ‹‹ከተፈጠረው አእዋፍ ሁሉ ለራስህ አንዲት ርግብ መረጥህ ከተፈጠሩት መንጋዎች ሁሉ ለራስህ
አንድ በግ መረጥህ›› ዕዝ.፫፣፳፮
-

የጥምቀት ጥቅም
1 ዳግመኛ በመወለድ የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅ ለመሆን
2 ለሥርየተ ኃጢአትና ለድኅነት
ድኅነትስ ከሻችሁ ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምናችሁ
ዩሐ 3÷5
ማር %6÷%6
ተጠመቁ ግብ ሐዋ 1÷'*
3 ለመንጻትና ለመቀደስ – እኛንም ዛሬ በኖኅ አምሳል በጥምቀት ያድናል፡፡ 1 ጴጥ 3÷&7

የጥምቀት ዓይነቶች
3 መክበሪያ አለን
 ቅዳሴ አትናቴዎስ 2÷&9
1 ክርስቶስን የምታስመስለን የከበረች ጥምቀት ናት
ሮሜ 7÷3
ይህች ጥምቀት አንዲት ናት
አሐቲ ጥምቀት- ጥምቀት አንዲት ናት
በአብ ስም በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ ስም ቢጠመቁ
- በአርባ በሰማኒያ ቀን በ $ በ * ዘመን ቢጠመቁ
- በዓብይ ባሕር በማዕከላዊ ባሕር በንዑስ ባሕር ቢጠመቁ
- በሊቀ ጳጳስ በኤጲስ ቆጶስ በቄስ እጅ ቢጠመቁ ጥምቀት አንዲት ናት አትደገምም
2 ባለሟል አድርጐ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ ከውስጥ የሚፈስ አንብዓ ንስሐ
3 የንስሐ ጥምቀት ዮሐንስ ሲያጠምቅ የነበረው ዛሬም በየጠበል ቦታ የምንጠመቀው
-
ለየት ያሉ ጥምቀቶች
ሀ. ደመ ሰማዕታት -ሰማዕታት ሣይጠመቁ አምነው በዐላውያን እጅ ቢሰየፉ
ደማቸው
ንስሐ ይሆንላቸዋል
ለ. በመከራ ጊዜ የሚደረግ ጥምቀት
ምሳሌ ሳራ ልጆቿን ጥምቀት ሣያገኙ እንዳይሞቱ ጡቷን በጥታ ደሟን
በመስቀል
አምሳል ቀብታቸው ጥምቀት ሆኖላቸዋል ( ስንክሳር ኅዳር@9
ሐ. የሐዋርያት ጥምቀት-በምሴተ ሐሙስ በሕጽበተ እግር በሲዖል የነበሩ ነፍሣት ጌታ ዓርብ የተወጋች ቀኝ እጁን
ባሳያቸው ጊዜ ተጠምቀዋል፡፡
ምሥጢረ ቁርባን
ቁርባን - በቁሙ፣ መንፈሳዊ አምኀ፣ ስለት፣
መሥዋዕት፣ መባዕ፣ ለአምላክ የሚሰጥ የሚቀርብ ገንዘብ
መሥዋዕተ ወንጌል - ጥሩ ስንዴና ወይን ከውኃ
በቀር ሌላ ጭማሪ የሌለበት
- በቁርባንነቱ ዕሙቅ ጥልቅ ረቂቅ ምሥጢር ያለበት
ማቁረብ - ማቀበል፣ መስጠት
በኦሪት - ቁርባን - የሥንዴ የወይን ወገን
መሥዋዕት - ከእንስሳት ከላም፣ከፍየል … ወገን
አንድም ቁርባን - የተሰዋው
መሥዋዕት - ያልተሰዋው ነው
መዝ $9*0
- በሐዲስ ኪዳን ቁርባንም መሥዋዕትም ሥጋውና ደሙ ነው፡፡
የቁርባን አመሠራረት
- በአልዓዛር ቤት ለራት ካመጡለት አንሥቶ ባርኮ ይህ ሥጋዬ ነው ይህ ደሜ ነው ብሎ
ሰጣቸው
ማቴ @6*@6
የቁርባን ጥቅም
1
የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የማታልፍ መንግስተ ሰማይን
ይወርሣል
- ካቶሊካውያን ደም የሌለው ሥጋ የለም ብለው ሥጋውን ብቻ ያቆርባሉ ይህ ኃይለ
ቃል ይመሰክርባቸዋል፡፡
- በዕለተ ምጽአት እኔ አስነሣዋለሁ
ቅዳሴ ማርያም ይህን ይበልጥ ያስረዳል
ማርያም ሆይ እንወድሻለን እውነተኛውን መብል እውነተኛውን መጠጥ
ወልደሽልናልና
እውነተኛ አለው - ከመስዋዕተ ኦሪት ሲለይ
- ያ ሥጋዊ ይህ መንፈሣዊ
- ያ ምድራዊ ይህ ሰማያዊ
- ያ አፍአዊ ይህ ውሳጣዊ





አንድም - የዚህ ዓለም ምግብ ማታ በልቶ ለጠዋት ጠዋት በልቶ ለቀን ያሻል
- የክርስቶስ ሥጋና ደም አንድ ጊዜ ከተቀበሉት በኅጢአት ካላሳደፉት
ለዘላዓለም ይበቃልና
አንድም- የዚህ ዓለም ምግብ ሞትን ያስከትላል ይህ ግን ሕይወት ይሆናልና
አንድም- ከአማናዊት ድንግል ስለተገኘ ፡፡
ዳግመኛ ከዕፀ ሕይወት
እንበላ ዘንድ አደለን እኛን ስለመውደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ስጋ
ክቡር ደሙ ነው (ውዳሴ ማር. ዘሐሙስ )
ቁጥር %6 - ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ ከእኔ ጋር ተዋህዶ ይኖራል እኔም
አድሬበት እኖራለሁ እንደ ብረትና እሳት የጸጋ ተዋህዶ

ለሥርየተ ኃጢአት
-
-
እንግዳ ሥርዓት የሚሆን የሐዲስ ርስት የመንግስተ ሰማያት መጽኛ የሚሆን በተሐድሶ ጸንቶ
የሚኖር ስለብዙዎች የሚፈስ ደሜ ይህ ነው ከሱ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው ኃጢአት ሊሠረይበት ሜቴ
6*@8
ሥጋውን ደሙን ለምን በመብል አደረገው ቢሉ
- መብል መጠጥ ከሰውነት ይዋሀዳልና
- እንደተዋሃደን ለማጠየቅ
- መብል መጠጥ ያፍቅራል እንዳፈቀረን ለማጠየቅ

በስንዴ በወይን ያደረገው በሌላ ያላደረገው
ትንቢቱ ምሳሌው ሉፈጸም ነው
- ትንቢት - ሲራ 4*@7
- የሰው ሕይወተ ነፍሱ ደመ ወልደእግዚአብሔር ነው ንስሐም ገብቶ ለተቀበለው ሰው ደስታ
ነው ደመ ወልደእግዚአብሔርን ለማይቀበል ምን ሕይወት አለው ሥጋው ደሙ ለሰው ደስታ
ተፈጥሯልና፡፡
- ደሙ ልበ ነፍስን ደስ ያስኛል አንድም ደሙ መስጠቱ ለከንቱ አይደለም ልበ ነፍስን ደስ ሊያሰኝ
ነው እንጂ
- ሥጋው ኃይለ ነፍስን ያጸናል
መዝ 3*!5
-
ምሳሌ - ወልከ ጼጼቅ በስንዴ በወይን ያስታኩት ነበርና
 ምሥጢሩ - ጌታችን እመቤታችን ሲበሉ የኖሩ ስንዴ ወይን ነበር፡፡ ፍጹም ሥጋውን ፍጹም ደሙን
እንደሰጠን ለማጠየቅ
 አንድም - በመሰለ ነገር ለመስጠት ስንዴ ስብ ወይን ደም ይመስላልና

በማር በወተት አለማድረጉ ፍት. ነገ. አንቀጽ !3
-
-
ማርና ወተት ጣዕማቸው የባሕርያቸው ነው መለኮት ሳይዋሃደው ሥጋ ብቻ አዳነ ያሰኛልና
ላም ሳር በልታ ወተት ንብም አበባ ቀስማ ማር ታስገኛለች ይህ ትርፍ ነው በሥጋው ደሙም ተረፈ
ኃጢአት አለበት ያሰኛልና
ላም አትበላዋ ቅጠል ሣር የለም ንብም አትቀስመው አበባ የለም፡፡ በሥጋው በደሙም የኃጢአት
ቅመም አለበት ያሰኛልና
-
ከማር ከወተት ተሐዋስያን አይርቁም ከሥጋው ደሙም አጋንንት አይርቁም ያሰኛልና

ርግብ ዋኖስም አይሁን፣ ላም በግ ፍየል አይሁን
-
-
ይህ አምሳል ነው አምሳሉ አልፎ አማናዊው ተፈጽሞ ሳለ አልተፈፀመም ያሰኛልና
እኒህ ሲያርዷቸው ይስማቸዋል በሰውት ቁጥር ይሰማዋል ያሰኛልና
እኒህ በዘር በሩካቤ ይገኛሉ እርሱም በዘር በሩካቤ ተወለደ ያሰኛልና
-
እኒህ መፍረስ መበስበስ አለባቸው በእርሱም ሙስና መቃብር አለበት ያሰኛልና
-
ምሥጢር ቁርባን ከጥምቀትና ከንስሐ በኋላ ይፈጸማል
- አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ያነጽሑ
- ››
››
››
›› ያጸርዩ
- ››
››
››
›› ይቄድሱ
- ያነጽሑ - ልብስ ከሣሙና ሲገናኝ
- ያጸርዩ - ሲለቀለቅ
- ይቄድሱ - ደርቆሲለበስ
- ከሳሙና እንደማገናኘት - ሰው ንስሐውን ይናገራል
- እንደመለቅለቅ - ንስሐውን ያደርሳል
- ደርቆ እንደመለበስ - ንስሐውን አድርሶ ሲወጣ ሥጋውን ደሙን
ይቀበላል
- ፍጹም ሥርየት የሚገኝ በሥጋው ደሙ ነው፡፡
-
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
ተንሥአ - ተነሣ
- ትንሣኤ - ጥሬ ዘር ሲሆን ትርጉም መነሣት
 ሞተ - ሞተ
- ሙታን /ሳድስው. ዘቅጽል በብዙ/
 ትንሣኤ ሙታን - የሙታን መነሳት ማለት ነው፡፡


ሰው እንደመላእክት ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲታመም እንዲሞት አልተፈጠረም

ሞት ሰው በገዛ ፈቃዱ ያመጣው ዕዳ ነው፡፡ ጥበብ ፩ ፣ !8__ − Ý@3
ሞት በአቤል ተጀምሯል
ትንሣኤ እንደለ በሄኖክ ነገረን
ዮሐ.አፈ.ድርሳን @2
ጌታችን ትንሣኤን ተነሥቶ አማናዊ አደረገው
ከዚህ አስቀድሞ እንደ ጌታ ያለ ትንሣኤ የተነሣ የለም ከእመቤታችን በቀር
ሌሎች ለጊዜው ቢነሱ ሞተዋል
በምጽአት በግርማ መለኮት በመጣ ጊዜ ሁሉም ለፍርድ ይነሣል፡፡







ከምጽአት በፊት ስለሚደረጉ ምልክቶች











እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ብዙዎች በኔ ስም ይነሣሉ ብዙዎችን ያስታሉ
ጦር ለጦር ጋሻ ለጋሻ ሲሳጎድ ገድሎ ሰልቦ ሲያገር ብትሰሙ እንዳትደነግጡ አስተውሉ
ሕዝበ ሮም በሕዝበ እስራኤል ላይ በጠላትነት ይነሱባቸዋል
በየሀገሩ ረሀብ ቸነፈር ይሆናል
ያን ጊዜ ለጸዋትወ መከራ አሣልፈው ይሰጧችኋል ከምኩራባቸው አስገብተው ይገርፏችኋል
ማቴ @4*3
በዚያን ጊዜ ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ይለውጣሉ
በመምህራን የሚያብሉ በመምህራን የሚያሣብሉ ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ ብዙ ሰዎችን
ያስቷቸዋል
ከሐሰትና ከኃጢኢት ብዛት የተነሣ ፍቅር ከብዙ ሰዎች ትጠፋለች
ወንጌል በአራቱ መዓዝን ትነገራለች በእስላም ቤት እንኳ ሣይቀር ትገኛለች፡፡
በሀገራችን ቴዎድሮስ በሀገራቸው ዮሐንስ ይነግሣል
በእስክንድርያ ሦስት ቀን ይዋጋሉ ዓራቱ ሊቃነ ጳጳሣት ለምን የክርስቲያን ደም በከንቱ ይፈሣል
ብለው መስዋዕት ይሰዋሉ የእንሰክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በስዋው ˝አነ ውእቱ ክርስቶስ ˝ ብሎ በርግብ
አምሣል ወርዶ ይመሰክራል ሃይማኖት አንድ ይሆናል በግቢ ይገናኛሉ፡፡ ( ገድለፊቅጠር፣ ራዕይ
ሲኖዳ )
በለስ ቅጠሉ የለመለመ ዓጽቅ ያወጣ እንደሆነ መከር እንደደረሰ ዕወቁ
 ያችን ዕለት ያቺን ስዓት የሚያውቃት የለም
 መላእክትም ሆነው ደቂቀ አዳምም ሁነው አያውቋትም ከብቻ ከአብ በቀር
 ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ
 ወልድ ቅድመ ተዋህደ አላዋቂ ሥጋን እንደተዋሃደ ለማጠየቅ
 አብ ለልጁ በመስጠት አውቋታል ወልድ ግን በሥራ አላወቃትም
 ወልድ ብቻ ያለ አብ አያውቃትም
ወልድ እንደሚያውቃት


ምሥጢረ ምጽአትን ሊያውቃት ሊመረምራት ገንዘብ ሊያደርጋት የተቻለው የለም

ከይሁዳ ወገን ከሚሆን ከዳዊት ባሕርይ የሚሆን ወልደእግዚአብሔር ነው፡፡
ምሥጢሪ ምጽኢትን ሊያውቃት ገንዘብ ሊያደርጋት ተችሎታልና
ዮሐ ራዕ 5*1 4


ሒሳዊ መሲሕ ማነው?





አባቱ ከነገደ ኤሣው ፤ እናቱ ከነገደ ዳን
አካሉ ቆቅሽማ ነው
አንድ ዓይኑ የሞተች ናት
አንድ ዓይኑ ደም የሰረበው ፈጣጣ ነው፡፡
ለበናም ነው

አውራ ጣቱ ጠማማ ነው
እግሩ ወለፎ ነው
ሰባቱ አርእስተ ኃጣውእ በእርሱ ጊዜ ይሠራሉ (ኃጢአተ አዳም፣ ቅትለተ አቤል፣ ጥቅመ ሰናዖር ፡
ኃጢአተ ሰዶም ፡ ኃጢአተ እስራኤል ፡ ቅትለተ ዘካራያስ ፡ ሞተ ወልደ እግዚአብሔር)
በሐሳዊ መሲሕ ለተመሰለው ምስል ያልሰገደ በእዋጅ ይገደላል
በግንባራቸው በቀኝ እጃቸው ዘመር ዘመስ ብለው እንዲጽፉ ያዛቸዋል
መርሞያዎዖስ – ሜሞ-$ ሞሜ $ ዔ-& ፌስ - 2 የሳን 3) ዋው 6 ዮድ -! ድምር 6)(6

በሰው ልክ ጅማት ያለው ሲሆን የዕለተ ዓርብ ፍጥረት ነው፡፡ ዮሐ ራዕ !3*1 !5





አመጣጡ ሰይጣን ብዙ ተአምር እያሳየለት ነው
- ድውይ በመፈወስ
- ምዉት በማስነሣት
- ጋኔን በማውጣት
 ፀሐይን ሳይይዝ የያዘ መስሎ ጨረቃን ሣይይዝ የያዘ መስሎ ይታያል 2ተሰ 2*9
በሐሳዊ መሲሕ መምጣት ታላቅ ጦርነት ይሆናል
 ባምስተኛው መንፈቅ አምስተኛው መልአክ ሥራውን በሠራ ጊዜ
 የሰበድአትን ከተማ በር የሚከፍትበት ቁልፍ /ሥልጣን ተሰጠው
 በአምስተኛው መንፈቅ መልአክ ሰብሮ ያወጣቸዋል መጥተው ያጠፋሉ

-







የአንበጣ መልክ አላቸው
መልክዐ አቃርብት እንዳላቸው ይሆኑ ዘንድ ስልጣን ተሰጣቸው
በሰው የሚያመጡት መከራ ጊንጥ በነደፈ ጊዜ እንዲያቅበዘብዝ እንደዚያ የሚያቅበዘብዝ ነው፡፡
ሰው ሊሞት ይወዳል አያገኝም
መልክአ አናብስት አላቸው
ዮሐ ራዕ 9*1
የእግራቸው ኮቲ አፍራስ እንደሚስቡት ሠረገላ መንካራኩር ነው
ከወደምሥራቅ የሚመጡ ነገስታት ጎዳናቸው ጥርጊያ ትሆን ዘንድ ውኃው ደረቀ ማለት ተከፈለ
/ደቂቀ ኬሬቢ ናቸው

ስለኃጢአታቸው አዝነው ብሔረ አዛፍ የገቡ ናቸው / ብሔረ ብፁዓን ማለት ነው/

ዕድሜያቸው ቪህ አመት ነው
በ3 ሩካቤ 3ት ልጆች ይወልዳሉ
- አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር ይሰጣሉ
- ሁለቱን ለዘር ይተዋሉ
ሲሞቱ መቃብራቸውን ቆፍረው ዘመዶቻቸውን ተሰነባብተው ይሞታሉ
ጌታ እሁድ እየገባ ያስተምራቸው ነበር
ኋላም ማቴዎስ ገብቶ አስተምሯቸዋል
ኋላም ዞሲማስ ከዳርና ዳር ዛፍ ገጥሞለት ገብቶ አይቷቸው ወጥቷል





እነዚህ ከሐሳዊ መሲሕ ጋር ተዋግተው ይሞታሉ፡፡
ራዕ !6*!2
 ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ዕለት ያስተምሩ ዘንድ
 - ሁለቱ ወዳጆቼን አዛቸዋለሁ /ኤልያስና ሄኖክ ናቸው)
 ሒሳዊ መሲሕ አምላክ አይደለም ብለው መስከረው ከፈፀሙ በኋላ ሐሳዊ መሲሕ ያስገድላቸዋል
-
በምሥጢር ሰዶም ግብጽ በምትባል አገር ያስጥለዋል /ኢየሩሳሌም/
 ሕዝብ አሕዛብም ሦስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ወድቆ ያዩታል /ቀባሪ ይከለክልባቸዋና/
 ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ነፍሳቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ታዝዛ መጥታ ታድርባቸዋለች ይነሣሉ
 ከዚህ በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ያርጋሉ
 ምድር እንደተዳመጠች ብራና ትሆናለች በስምንቱ ነፋሳተ መዓት ከተመታች አስክሬን ከጸዳ በኋላ
ዮሐ ራዕ !1*
 ወልደ እግዚአብሔር በደብረ ጽዮን ቆሞ አየሁ /ድል ነስቶ/
 ከእርሱ ጋር አሥራ አራት ዕልፍ ከአራት ቪ ሰማዕታት ሕፃናት ድል ነሥተው አየሁ በግንባራቸው /በገጸ
ልቦናቸው/ ስመ ወላዲ ስመ ተወላዲ ስመ ሠራፂ የተፃፈባቸው
 ሬሳቸውን
 ከወደ
ሰማይ እንደመሰንቆ ያለ ቃል ሰማሁ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ እያሉ ሲያመሰግኑ ከነዚህ መዓርግ
ያልደረሰ ምስጋናውን የሚያውቅ የለም፡፡
-

በጉን ወደሄደበት የተከታተሉት /አብነት/ ያደረጉት
ማዕከላዊ ወንበር ይዘረጋል ጌታ በዚያ ላይ ይቀመጣል፡፡
የሙታን አነሳስ
- መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለምዉታን ብሎ ሲያመሰግን
- በመጀመሪያ አዋጅ
- ከአራቱ መዓዝን የተበተነ አካለ ሥጋ ይሠበሰባል
- ጻድቁም ጻድቁን ኃጥኡም ኃጥኡን መስሎ ይነሳል
- በባሕር፣ በየብስ ያለው አንድም በውቅያኖስ በዚህ ዓለም ያለው
- አራዊት የበሉት የሠው ሥጋና የአውሬ ሥጋ የተለያየ ስለሆነ
- ነፍስ ከሥጋው ከተለየችበት፣ ራሱ ከወደቀበት፣ እትብቱ ከተቆረጠበት የእንግዴ ልጅ ከተቀበረበት
 በሁለተኛ አዋጅ
- አጽም ከሥጋ ጋራ አጥንትና ጅማት ይያያዛሉ
- መንቀሳቀስ ሳይኖር ፍፁም በድን ይሆናል፡፡
 በሦስተኛው አዋጅ
- ሙታን ነፍስ ከሥጋ ተዋሕደው ፈጥነው ይነሣሉ፡፡
- በዚህ ዓለም የሠሩት በጎውንም ክፉውንም ሥራቸውን ይዘው












ወዳጆችህን በምስጋና ቃል ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግስተ ሰማይን ትወርሱ ዘንድ
ብራብ አብልታችሁኛልና፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛልና፣ እንግዳ ብሆን ተቀብላችሁኛልና፣ ብታሰር
ጠይቃችሁኛልና ብታረዝ አልብሳችሁኛልና
ወደኃጥአን ተመልሰህ በወቀሳ አነጋገር የዲያብሎስ የጌባል የይሁዳ የአዳም መርገም ያደረባችሁ
ለዲያብሎስ ለአጋንንት ወደ ተዘጋጀ ወደ ገሃነም ሂዱ ትላቸዋለህ
ያን ጊዜ ክደት ተንኮል ዓመድ የሚናገር አንደበት ሁሉ ምላሽ ያጣል
የማይረባ የማጠቅም ኃዘን ይደረጋል
እንባ ፍጻሜ እንደሌለው እንደክረምት መሌ በዝቶ ይፈሳል
ፈጣን መብረቅ የሚያስደነግጥ የነጎድጓድ ቃል ይሠማል
ነፍስ ከሥጋ የሚለይ ረቂቅ ትእዛዝ ይታዘዛል
 ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ምዕራፍ 2÷&3 -'
ያን ጊዜ አጭር ረጅም የለም
ወንዱ በዓቅመ አዳም ሴቷ በዓቅመ ሔዋን የ' የ%5 ዓመት ሆነው ይነሣሉ
ያን ጊዜ ቀይ ጥቁር የለም ሁሉ አንድ አካል አንድ መልክ ነው እንጂ
ጻድቃን ክርስቶስን መስለው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ይነሣሉ፡፡ ቅዳሴ አትናቴዎስ 3÷'1





የበለጠ ለማስረዳት አክሲ ማሮስ ዘሠሉስን ተመልከት
ያን ጊዜ አንዱ ለአንዱ ቤዛ ሆኖ መሄድ የለም ቅ. አትናቴዎስ 3÷'2
ወደ ሲኦል ወደገሃነም ሲወርዱ ባያቸው ጊዜ እሱ ቅሉ ፈጣሪ በቃሉ በእጁ ስለፈጠራቸው ፍጥረቶች
እስኪያለቅስ ድረስ
ከሚያለቅስላቸው አይምራቸውም ቢሉ ፈታሒ በጽድቅ ነውና ይፈርድባቸዋል መሐሪ ሩህሩህ ነውና
ያዝንላቸዋል፡፡
የትንሳኤ ሙታን ምሳሌዎች








ከመጽሐፍ ቅዱስ፡ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ )9፡1
ሄኖክ ማረጉ የትንሣኤያችን ምሳሌ ነው፡፡
ዕብራ ፲1÷ ፭
ኖኅም እግዚአብሔር አዞት መርከብ ሠራ ዳግመኛ ከመርከብ መውጣትን ለወገኖቹ አደረገ
6÷03 - &2
ወደ መርከብ መግባታቸው የመሞታችን መውጣታቸው የመነሳታችን ምሳሌ
ሙቀት ልምላሜ በተለያቸው በአብርሃምና በሣራ ተስፋ ትንሣኤን አስረዳ

ዘፍ 08 ÷ 9 -04
ያዕቆብም አጽሙ በግብፅ እንዲቀር አልወደደም ይዛችሁኝ ውጡ አሉ፡፡
ትንሣኤን ለማስረዳት
ግብጽ የመቃብር ከንዓን የትንሣኤ ምሳሌ ናትና
ዘፍ

- እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ የያዕቆብ አምላክ ነኝ በማለቱ ትንሣኤን አስረዳ
ዘጸ.፫፣፮
- ከብዙ ዘመን ጀምራ ደርቃ የነበረች የአሮን በትር መለምለሟ- ትንሣኤን ታስረዳለች
- ኤልሳቤጥ በመጽነሷ ትንሣኤን አስረዳ
ሉቃ 1÷&3

በትር የሆነች እባብ እባብ የሆነች በትር ያገለገለ ሥጋ በትንሣኤ እንደሚነሣ አስረዳች

ሮቤልን እሻዋለሁ ይዳንልኝ እንጂ አይሙትብኝ፡፡ በሞተ በ203 አመቱ ይዳንልኝ ማለቱ ትንሣኤ
ሙታን እንዳለ አውቆነው
የሮቤል አጽም መጥቆሩ የመሞታችን ነጭ መሆኑ የመነሣታችን ፡፡
ይዳንልኝ - የትንሣኤ አይሙትብኝ - የመሞታችን
ኤልያስ የሰራፕታዋን ሴት ልጅ መላ አካሉን አስነሣ ከሙታንም ተከፍሎ የሚቀር አካል የለም
ግዙርነትና ቆላፍነት ትንሠኤን አይከለክሉም ሄኖክ − ቆላፍ ፣ ኤልያስ - ግዙር ነውና
ደናግል መዓስባንም ይነሣሉ
ኤልያስ ሄኖክ ተነስተዋልና
ሙታን ይነሣሉ በሲኦል ያሉትም ይድናሉ
ኢሳ &6÷%9
በውኑ የሞተ ሰው አይነሣምን
ኢዮ
ራሱ ያለበትን ዕትብቱ የተቀበረበትን አንድም ልጅነት ያገኘበትን ቦታ ያይ ዘንድ አንድም ሥጋውን
ይዋሃድ ዘንድ











ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ትለያለህ ሙተው ወደ መሬት ይመለሳሉ ዳግመኛ ነፍስ ታሳድርባቸዋለህ
ይፈጠራሉ ማለት ተዋህደው ይነሳሉ

ከ7ት ቀን በኋላ ምድር የሚቆምባት ቋሚ ሰው አጥታ ባዶዋን ትቀራለች፡፡

ታይቶ የማያውቅ ዓለም ይታያል የሚፈርስ የሚበሰብስ ሰው የኖረበትም ዓለም ያልፋል
ዕዝራ ሱትኤል
የፀነሰች ሴት የምትወልድበት ቀኗ 9 ወር ከደረሰ በኋላ በማህፀኗ ያለውን ፅንስ ይዞ ማስቀረት
ይቻላት እንደሆነ ጠይቃት አለኝ
ሴት ምጥ ተይዛ ለመውለድ እንድትቸኩል ምድርም ከአቤል ጀምሮ በሷ የተቀበሩትን ለመስጠት
ትቸኩላለች
ዮሐ ራዕ
ቦታይቱ አዕጽምትን የተሞላች ናት አዙሮ አሳየኝ በ4ት መዓዝን ሞልተዋል አጥንቶቹ ፈርሰው
በስብሰው ነበር
ተናገርሁ እነሆ ንውጽውጽታ እነዚያ የረገፉ አጽሞች ተገናኙ መዓርገ ሥጋን ተዋህደው በላይ
ቁርበትን ለብሰው አየሁ ሕዝቅኤል '7÷1 -%6
እነዚህም ሕዝቅኤል ያስነሳቸው 6ሺ ሙታን ናቸው፡፡
እነሱን እንደሙታን ባቢሎንን እንደ መቃብር ኢየሩሳሌምን እንደትንሣኤ አድርጎ ተናገረ፡፡
ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ ሁለተኛ አይሞቱም ፡፡







- ተፈጥሯዊ











-
የትንሣኤ ምሳሌ
እነሆ ፍጥረት ሁሉ የትንሣኤን ነገር ያስረዳል
ፀሐይ በገባ ጊዜ እንተኛለን ሌሊቱ አልፎ ፀሐይ በወጣ ጊዜ እንነሣለን
ፀሐይ እንዲወጣ እንወዳለን በዚህ ዓለም ሲያበራ እንዲውል በዚህ ዓለም እንኖራለን
እንዲገባ እንሞታለን፡፡ ተመልሶ እንዲወጣ በትንሣኤ ዘጉባኤ እንነሣለን፡፡
በእርሻ የሚዘራ ዘር እንዲታጨድ እንዲቆረጥ እንሞታለን እንዲዘራ እንቀበራለን
ከተዘራ በኋላ እንደገና እንዲበቅል እንነሣለን
አንበጣም ከሞተ በኃላ ከምድር ይነሣል
የራሳችን ጌጥ እንደሆነ የምናስበው ፀጉራችን ይላጩታል ባይሆን ይቆርጡታል ጥፍሮቻችን
ይቆርጧቸዋልና ዳግመኛ ይበቅላሉና ትንሣኤን ያስረዳሉ፡፡
የእሳት ራት ከ( ቀን በኃላ፣ ፍልፈል ከ6 ወር በኋላ ይነሣሉ
የእበት ትል ፡ሺህ እግር ፈርሰው በስብሰው ኖረው ዳግመኛ ይነሣሉ እንዲሞቱ እንሞታለን እንዲነሡ
እንነሣለን
ኦፈ ፊንክስ /ንስር/ ፈጽሞ ትንሣኤን ያስረዳል
 መንግስተ ሰማይ
ማን እንደሆነች ከሥነ ፍጥረት ዘአሁድ ተመልከት
መንግስተ ሰማይ
- ማን
እንደሆነች ከሥነ ፍጥረት
ዘአሁድ ተመልከት !