Transcript Slide 1

እንኳን
ደስያለን
ደስያላችሁ
1. አደረጃጀትና ሥያሜ
- ክልል ………… ዋና ዳይሬክተር
….......... ም/ዳይሬክተር
…...........ዳይሬክተር/ ባለሙያና ባለቤት
-ዞን ……........... በ3
………….. ቅ/ጽ/ቤት
………….. ሥራ አስኪያጅ
……........... አስተባባሪ
……........... ባለሙያና አስተባባሪ
-ከተማ/ወረዳ …… በ3
….. ጽ/ቤት
….. ጽ/ቤት ኃላፊ
…… አስተባባሪ
…… ባለሙያና አስተባባሪ
- ቀበሌ …………… በ3 ከተሞች
2.የሥራ መደቦች ብዛት
•
•
•
•
ክልል ……95+4
ዞን ………36+2
ከተማ ……39+2
ወረዳ …… 23+1
ቀበሌ …… 15
33+2
31+2
23+1
27+2
27+1
23+1
3. የሰው ኃይል መረጃ
ተ.
ቁ
የሥራ ሂደት
1
•
ክልል
ዞን
1ኛ
2ኛ
ከተማ
3ኛ
1ኛ
2ኛ
ወረዳ
3ኛ
1ኛ
2ኛ
ቀበ
3ኛ ሌ
ዋና ዳይሬክተር
4+1
2+1 2+1 2+1 2+1
2+1 1+1 1+1 1+1 1+1
2
ም/ዳይሬክተር
2+1
4
4
4
4
1
1
1
1
4
3
የግ/ት/የህ/ግ/
10
9
7
5
19
17
12
11
9
7
3
ገቢ/አ/ክ/
13
8+1 7+1 5+1 11+1
6+1 -
-
-
-
4
ኦዲ/ህግ/ማስ
11+2
1
11
1
2
2
2
10
10
0
5
የኢ/ኮ/ቴ/
9
4
14
4
4
3
3
2
2
2
6
የሰ/ኃ/ሥ/አ/
16
3
13
3
2
1
1
1
1
1
7
የዕ/ክ/ግ/ገ/ጥ
7
3
3
3
2
1
1
1
1
1
7
የግ/ፋ/ንብ/አስ
19
10
10
10
10
10
10
10
10
10
8
የውስጥ ኦዲት
4
1
1
1
1
1
1
1
1
1
9
ደንበኛ
1/
64+4
1/
44
1
1
1
1
1
1
1
1
15
4. የደመወዝ ስኬል አደረጃደት
ደረጃ
ከፍታ
የትም/ደረጃና የአገልግሎት
ዘመን
12ኛ
መነሻ
ደመወዝ
10+2 +4
የእርከን ደመወዝ
1 2
ጣሪያ
3 4
I
0
520
1.444
II
2
613
1.942
III
4
920
2.593
1,306
1,751
3.369
V
0
2
VI
4
2,367
5.263
VII
6
3,098
6.389
IV
4.269
VIII
2
3,973
7.697
IX
4
4,928
9.131
X
6
6,008
10.792
XI
8
7,237
12.453
Xll
10
8,640
14.114
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት የገቢዎች ባለሥልጣን
የሠራተኞች ድልድል መመሪያ ቁጥር
2/2003
የሠራተኞች የድልድል መመሪያ ለምን
በቅድሚያ ለየሥራ ሂደቶችና ለሥራ መደቦች ሁለንተናዊ
ብቃት
 መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸውና
የሕዝብ አገልጋይነት ስሜት የተላበሱ ሠራተኞችን
 በፍትሃዊነት ለይቶ ለመደልደል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት
በማስፈለጉ፣ እንዲሁም
 ሠራተኞችን የመመልመል፣ የመመደብ፣ የማሰማራትና
የማሰናበት ተግባርን በሚያስተዳድርበት በሰራተኞች አስተዳደር
ደንብ መሠረት ይህ የሠራተኞች የድልድል ማስፈጸሚያ
መመሪያ ወጥቷል፡፡
•
ርዕስ
ይህ መመሪያ በአብክመ የገቢዎች ባለስልጣን ሠራተኞች
የድልደላ መመሪያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም
ካልተሰጠው በስተቀር ከዚህ በታች ያሉት ቃላትና ሐረጐች
የሚከተለው ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡
1.«ድልደል» ማለት በዚህ መመሪያ መሠረት የባለስልጣኑን አዲስ
የአደረጃጀት መዋቅር ሰነድ
በማድረግ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም የሰው ኃይል ስምሪት ነው ፡፡
2.« ባለስልጣን » ማለት የአማራ ክልል ገቢዎች
ባለስልጣን ነው፡፡
3.« ቅርጫፍ ጽ/ቤት » ማለት በዞን አስተዳደር ደረጃ
የሚገኝ የገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ነው፣
4.« ጽህፈት ቤት » ማለት በከተማ እና በወረዳ አስተዳደር እርከኖች ደረጃ
የሚገኝ የገቢዎች ጽ/ቤት ነው፣
5. የታክስ ማዕከል” ታክስ ከፋዬች በሚገኙበት አካባቢ እንደ አስፈላጊነቱ
በከተማ አስተዳደሮች ሥራ የሚገኝ የታክስ መሰብሰቢያ ጣቢያ ማለት
ነው ፡፡
6.« ዋና ዳይሬክተር »ማለት የአማራ ክልል ገቢዎች
ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ነው፡፡
7. “ምክትል ዳይሬክተር” የአማራ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን
ምክትል ዳይሬክተር ማለት ነው።
8. “ዳይሬክተር” በክልል ደረጃ የስራ ሂደትች ዳይሬክተር ማለት
ነው።
9. “ስራ አስኪያጅ” ወይም “የጽ/ቤት ኃላፊ” ማለት እንደቅደም
ተከተሉ የዞን ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ስራአስኪያጅና የከተማ ወይም
የወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ማለት ነው።
10.« የሥራ ሂደት አስተባባሪ » ማለት በዞን፣ በከተማ፣ ወረዳና
በቀበሌ ገቢ ጽ/ቤቶች በሚገኝ አንድ የሥራ ሂደት ከአምስት
ያላያነሱ ፈጻሚዎች ያሉበት የሥራ ሂደት ባለሙያና
አስተባባሪ ማለት ነው፡፡
11.« የሥራ ሂደት ባለሙያና አስተባባሪ» በዞን፣ በከተማ፣ በወረዳ
እና በቀበሌ ገቢ ጽ/ቤቶች በሚገኝ አንድ የሥራ ሂደት
ከአምስት ያነሱ ፈጻሚዎች ያሉበት የሥራ ሂደት ባለሙያና
አስተባባሪ ማለት ነው፡፡
12.«የበላይ አመራር» ማለት በክልል ዋና ዳይሬክተር
እና ም/ዳይሬክተር& በዞን ቅ/ጽ/ቤቶች ስራ
አስኪያጅ፣ በከተማ እና በወረዳ የገቢ ጽ/ቤቶች
የጽ/ቤት ኃላፊ ማለት ነው፡፡
13.«የሥራ ሂደት» ማለት በባለስልጣኑ የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ
ግብአትና መረጃን ተጠቅሞ ውጤት ለማምጣት በአንድ ሠራተኛ
ወይም የሥራ ቡድን ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተያያዥነትና
ተከታታይነት ያላቸው የሥራ ተግባራት የሚከናወኑበት የአንድ
ክፍል ወይም ንዑስ ክፍል የሥራ ፍሰት ነው፡፡
14.« ሠራተኛ » ማለት በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኝ የሥራ ሂደት
ዳይሬክተር፣ አስተባባሪና ፈጻሚዎችን የሚያጠቃልል ሲሆን
የመንግስት ተሚዎችን አይጨምርም፡፡
15.«የሠራተኛ ደልዳይ ኮሚቴ» ማለት የሥራ ሂደቶችን የሰው
ኃይል ፍላጐት በመለየት እና መሠረት በማድረግ ሠራተኞችን
በመደልደል በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ የበላይ አመራሮች
የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ በዚህ መመሪያ የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡
16. የቅሬታ አጣሪ ቡድን ” የምደባ ዓላማውን መሰረት
በማድረግ ከሠራተኛ ድልደላው መጠናቀቅ በኋላ
ከሠራተኞች የቀረበለትን ቅሬታ መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ
ለማቅረብ የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡
17. በዚህ መመሪያ በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ፆታም
ያገለግላል ፡፡
ክፍል ሁለት
3. የሠራተኞች ድልድል የአፈጻጸም ቅደም ተከተል
1.
ዋና ዳይሬክተሩ የክልል የሥራ ሂደት ዳይሬክተሮችን ይሰይማል፡፡
እንዲሁም የዞን ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ የከተማ እና
የወረዳ ገቢ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ሹመት መሰጠቱን ያረጋግጣል፡፡
2.
በየደረጃው የተሾሙ የዞን ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆች እና
የወረዳ እና የከተማ የገቢ የጽ/ቤት ኃላፊዎች በየአስተዳደር እርከኑ
ከሚገኙ አስተዳዳሪዎች እና በየደረጃው ከሚገኝ የላይኛው እርክን
የገቢ ተቋም ኃላፊ ጋር በመመካከር የሥራ ሂደት አስተባባሪዎችን
ይሰይማሉ፡፡
3. የበላይ አመራሩ ከሥራ ሂደት ዳይሬክተሮች፣ አስተባባሪዎችና
የሥራ
ሂደት
ባለሙያዎችና
አስተባባሪዎች
እና
እንደአስፈላጊነቱ ከሌሎች ሠራተኞች የተውጣጣ ከ3 እስከ 5
አባላት ያሉት የሠራተኛ ደልዳይ ኮሚቴ አባላትን ይሰይማል፡፡
ከኮሚቴ አባላት መካከልም የኮሚቴውን ሰብሳቢና ፀሐፊ
ይሰይማል፡፡
4. የበላይ አመራሩ በጠቅላላ ሠራተኞች ጉባዔ ሁለት የሠራተኛ
ተወካዬችን በማስመረጥ የሠራተኞች ደልዳይ ኮማቴ አባላት
እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ በገቢ ጽ/ቤቱ ሴት ሠራተኞች ካሉ
ከሠራተኛ ተወካዬች መካከል አንዷ ሴት ትሆናለች፡፡
5. የሠራተኛ ተወካዮች ኃላፊነታቸውን በብቃት የሚወጡ፣
በመልካም ሥነ-ምግባራቸው አርአያ የሆኑ ከቡድንተኝነትና
ከአድሎ የጸዱ፣ የኮሚቴውን ሚስጥር የሚጠብቁ እና
በመ/ቤቱ ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገሉ መሆን አለባቸው፡፡
6. የሠራተኞች ድልድል የሚካሄደው ሠራተኞች አሁን በስራ
ላይ በሚገኙባቸው የሥራ ሂደቶች ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 የተደነገገው ቢኖርም
ሠራተኞች በያሉበት ሂደት ተወዳድረው ምደባው ከተጠናቀቀ
በኋላ የሥራ ምደባ ያላገኙ ሠራተኞች ብቻ ዝቅተኛ ተፈላጊ
ችሎታውን በሚያሟሉባቸው ሌሎች የሥራ ሂደቶች
ተወዳድረው እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡
8. የሠራተኞች ድልድል የሚካሄደው ከከፍተኛ የሥራ ደረጃ
በመጀመር ይሆናል፣
9. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 8 የተደነገገው ቢኖርም
የሠራተኞች ምደባ የሚካሄደው ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታን
በማሟላት ብቻ ሳይሆን የስራ መደቡን ዝርዝር ተግባራት
በአግባቡ ይፈጽማሉ ተብሎ ከታመነ ብቻ ይሆናል፡፡
7.
4. በሠራተኞች ድልደላ ወቅት የሚከናወኑ ተግባራት
1 የበላይ አመራር
ሀ/ ለስራ መደቡ የተቀመጠውን ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ
የሚያሟሉ የስራ ሂደት ዳይሬክተሮችን እና/ወይም አስተባባሪዎችን
ይሰይማል፡፡
ለ/ ዳይሬክተሮች፣ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የሥራ ሂደት ባለሙያና
አስተባባሪዎች እና አንደአስፈላጊነቱ ሠራተኞች እንዲሁም የሠራተኛ
ተወካዮች ያሉበት የሠራተኛ የደልዳይ ኮሚቴ አባላትን ይሰይማል፡፡
ሐ/ በጠቅላላ ሠራተኞች ጉባዔ ሁለት የሠራተኛ ተወካዬችን በማስመረጥ
የሠራተኞችን የደልዳይ ኮሚቴ በማደራጀት ሥራ ያስጀምራል፣
መ/በሠራተኞች የድልድል መመሪያ ላይ ከሠራተኞች ጋር
ውይይት ያካሂዳል፡፡ በመ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳም ይፋ
እንዲሆን ይደረጋል፣
ሠ/ ከደልዳይ ኮሚቴው ለሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች የመጨረሻ
ውሳኔ ይሰጣል፣
ረ/ በኮሚቴ አባላት መካከል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሮ መፍታት
ባለመቻሉ ከኮሚቴው ሪፖርት ሲቀርብ ውሳኔ ይሰጣል፣
ሰ/ የሠራተኞች ድልድል እንደተጠናቀቀ በመ/ቤቱ
የማስታወቂያ ሰሌዳ ይፋ እንዲሆን ያደርጋል፣
ሸ/ የሥራ መደብ ለተሰጣቸው ሠራተኞች የምደባ
ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ያደርጋል፣
ቀ/ ከምደባ በኋላ የሚነሉ ቅሬታዎችን የሚያጣራ የቅሬታ ሰሚ ቡድን
ያቋቁማል፣
በ/ የቅሬታ ሰሚ ቡድኑ በሚያቀርባቸው የውሳኔ ሃሳቦች ላይ የመጨረሻ
ውሳኔ ይሰጣል፣
2. የሠራተኞች ደልዳይ ኮሚቴ
ሀ/ በሠራተኞች ፊት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሃቀኛነትና በታማኝነት
ለመወጣት ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ
ለ/ የሥራ መርሃ-ግብር አዘጋጀቶ ለመ/ቤቱ የበላይ አመራር በማቅረብና
በማስፀደቅ ሥራውን በቅንነትና በታማኝነት ያካሂዳል፣
ሐ/ የሠራተኞችን የድልደላ መመሪያ በማስታወቂያ
ሰሌዳ ይፋ ያደርጋል፣
መ/ በየስራ ክፍሎች ተመድበው እየሰሩ የሚገኙ
ሠራተኞችን የትምህርት ደረጃ የአገልግሎት ዘመን እና የማህደር
ጥራት መረጃዎችን ያደራጃል፣
ሠ/ ሠራተኞች ስለራሳቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድ እና
የማህደር ጥራት መረጃዎች ትክክለኛነት በፊርማቸው
እንዲያደረጋግጡ ያደርጋል፣ ተጨባጭ ቅሬታዎች ወይም/እና
ጥቆማዎች ካሉ ተቀብሎ ይመረምራል፣ ስህተት ካለም
ያርማል/ ያስተካክላል፣
ረ/ ኮሚቴው በአብላጫ ድምጽ ይወስናል፡፡ ሆኖም የኮሚቴው
ጽምጽ እኩል ከመጣ ሰብሳቢው ያለበት አብላጫ ድምጽ
ተደርጐ ይወሰዳል፣
ሰ/ በኮሚቴው አባላት መካከል የሃሳብ ልዩነት ከተፈጠረና መፍታት
ካልተቻለ የሃሳብ ልዩነቱን መዝግቦ ለመ/ቤቱ የበላይ
አመራር በማቅረብ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፣
ሸ/ በሠራተኞች የድልድል መስፈርት መሰረት በየሥራ ሂደቱ
ሠራተኞችን በትም/ደረጃቸው፣ በአገልግሎት
ዘመናቸው፣
በማህደር ጥራታቸው እና በሥራ ተነሳሽነታቸው በማወዳደር
የምደባ የውሳኔ ሃሣብ ለበላይ አመራሩ ያቀርባል፡፡
ቀ/ በበላይ አመራሩ የፀደቀ የሠራተኞች የድልድል ውጤቱ በይፋ
ለሠራተኞች እስኪገለጽ ድረስ ሥራውን በሚስጥር ያከናውናል፣
ሰለድልደላው ሂደትም በየዕለቱ ለበላይ አመራር ሪፖርት
ያቀርባል፣
በ/ ኮሚቴው በሠራተኞች ድልድል ወቅት ለሚፈጠሩ ስህተቶች/ ችግሮች
እንደ ቡድንም ሆነ በተናጠል ተጠያቂ ነው፣
ተ/ በሠራተኞች ድልድል ወቅት ችግሮች ሲያጋጥሙ
ችግሮች የሚፈቱበትን አቅጣጫ ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ይፈጽማል፣
ቸ/ የሠራተኞች ድልድልን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ያጠናቅቃል፣
ነ/ የሠራተኛ ድልደል ተልኮውን ሲያጠናቅቅ ለሥራው የተጠቀመባቸውን
ሰነዶች በሙሉ ከተሟላ
ሪፖርት ጋር በመ/ቤቱ ለተደራጀ የሰው
ኃይል ሥራ አመራርና ልማት የሥራ ሂደት ያስረክባል፣
3. የተቋሙ ሠራተኞች
ሀ/ ስለራሳቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድ እና የማህደር ጥራት
ማስረጃዎች ትክክለኛነት በፊርማቸው ማረጋገጥ፣
ለ/ ለድልድል ሥራው ሊጠቅሙ የሚችሉ ተጨባጭ መረጃዎችን ወይም/ እና
ጥቆማዎችን ለደልዳይ ኮሚቴው ማቅረብ ፡፡ ሆኖም ትክክለኛ ያልሆነ
መረጃ አቅርቦ የተገኘ ሠራተኛ አግባብ ባለው ህግ ይጠየቃል፣
ሐ/ ስለራሳቸውም ሆነ ስለሌሎች ሠራተኞች መረጃ ሲጠየቁ በቅንነት
የሚያውቁትን ትክክለኛ መረጃ መስጠት፣
መ/ ሌሎች ሠራተኞች የተሳሳተ መረጃ አቅርበው በማይመጥናቸው
ቦታ እንዳይመደቡ መታገልና
ማጋለጥ፣
ሠ/ ከአሉባልታና የምደባውን ተግባር ከሚያደናቅፉ ሌሎች
ተግባሮች እራሳቸውን ማራቅ፣
ረ/ በጠቅላላ ሠራተኞች ስብሰባ መሳተፍ፣
4. የሰው ኃይል ሥራ አመራርና ልማት
የሥራ ሂደት
ሀ/ በየደረጃው በሚገኙ የገቢ ጽ/ቤቶች የተደራጀ የሰው ኃይል
ሥራ አመራርና ልማት የሥራ ሂደት ከመ/ቤቱ የሰራተኞች
የደልዳይ ኮሚቴ ሰነዶችን ይረከባል፣ አደራጅቶ በአግባቡ
ይይዛል፡፡ አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅም ሰነዶችን ያቀርባል፣
ለ/ የሥራ መደብ ለተሰጣቸው ሠራተኞች የምደባ ደብዳቤ
እንዲደርሳቸው ያደርጋል፡፡
ሐ/ በክልል ደረጃ ያለው የሰው ኃይል ስራ አመራርና ልማት የስራ
ሂደት በአንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 2/ከመ እስከ ረ የተጠቀሱት
ተግባራትን ይከናወናል፡፡
ክፍል ሶስት
5.የሠራተኞች የድል ድልመስፈርቶችና
የተሰጣቸው ክብደት
ተ.ቁ
1
አንፃራዊ
ክብደት
በ(%)
የምዘና ባህሪያት
የትምህርት ዝግጅት
( 20%)
 የትምህርት ዝግጅቱ በጥናቱ ላይ የተመለከተ
ከሆነ
20
 የትምህርት ዝግጅቱ በጥናቱ ላይያልተመለከተ
ሆኖ ነገር ግን በተዘዋዋሪ አግባብ ያለው ወይም
ተቀራራቢ ከሆነ፣
15
 የትምህርት ዝግጅቱ አግባብ የሌለው ከሆነ
ከውድድር ውጭ ይደረጋል
0
የመረጃ
ምንጭ
የቀረበ የትምህርት
ማስረጃ ወይም
የግልማህደር
ተ.ቁ
2
አንፃራዊ
ክብደት
በ(%)
የምዘና ባህሪያት
የሥራ ልምድ
( 10%)
 አስር ዓመትና በላይ የስራ ልምድ
10
ከአምስት ዓመት በላይና ከአስር
ዓመት መታች
7
 እስከ አምስት ዓመት የስራ
4
ልምድ ያለው
የመረጃ
ምንጭ
የቀረበ የሥራ
ልምድ ወይም
የግልማህደር
ተ.ቁ
3.
አንፃራዊ
ክብደት
በ(%)
የምዘና ባህሪያት
የማህደር ጥራት
( 5%)
 ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ ማድረግ
 ከአንድ ወር በላይ እስከ ሶስት ወር ቅጣት
0
እስከ አንድ ወር ደመወዝ ቅጣት
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቅጣት
 የቃል ማስጠንቀቂያ ቅጣት
2
 ምንም የቅጣት ሪከርድ የሌለበት
5
1
3
4
የመረጃ
ምንጭ
የግል ማህደር
ተ
.
ቁ
አንፃራዊ
ክብደት
በ(%)
የምዘና ባህሪያት
4 ለለውጥ ያለው ተነሳሽነትናዲሞክራሲያዊነት
.  አዳዲስ ሃሳቦችን ለማወቅ ጥረት የሚያደርግና መንግስት
ያወጣቸውን ፖሊሴዎችናስትራቴጅዎች የተቀበለ
(25%)
7
 በሥራ ላይ የሚያሳየው ተባባሪነት፣ በቡድን ለመስራት
ያለው ፈቃደኝነትና አቅም
የመረጃ
ምንጭ
6
 የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራሙና የታክስ
ሥርዓት ማሻሻያ ኘሮግራምን ተቀብሎ ለመተግበር
የሚያደርገው እንቅስቃሴ
7
 ከቆዩና ጊዜ ካለፈባቸው አመለካከቶች የጸዳ
5
ደልዳይ
ኮማቴ
ተ.ቁ
5.
የምዘና ባህሪያት
አንፃራዊ
ክብደት
በ(%)
መልካም ሥነ-ምግባር ያለው
(15%)
 ለተቋሙ ሀብትና ንብረት የሚያሳየው
ተቆርቋሪነት
3
 በሥራው ላይ ታታሪ የሆነና በሌሎች
ዘንድም በአርያነቱ የሚታወቅ
5
 ከአጉል ሱሶች የጸዳ
3
ከአሉባልታና ከቡድንተኝነት የራቀ
4
የመረጃ
ምንጭ
ደልዳይ
ኮማቴ
ተ.ቁ
6.
አንፃራዊ
ክብደት
በ(%)
የምዘና ባህሪያት
አገልግሎት አሰጣጥ
(25%)
 የውስጥና የውጭ ተገልጋዮችን በጥናቱ
በተቀመጡ የአሰራር ሥርዓቶች መሠረት
ለማስተናገድ ያለው ብቃትና ፍላጐት
10
 ሥራውን ለመፈጸምና በሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን
ለመፍታት ያለው ብቃት
5
ተገልጋዮችን በትህትና ማስተናገድ
5
 ሥራን በጥራት በፍጥነት ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ
መስራትና የስራ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም
5
ድምር
100%
የመረጃ
ምንጭ
ደልዳይ
ኮማቴ
ክፍል አራት
6. በሠራተኞች ድልደል ጊዜ ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ቁልፍ
ጉዳዩች
1. አንድ ሠራተኛ ለሚወዳደርበት የሥራ መደብ በአዲሱ
የአደረጃጀት መዋቅር የተቀመጠውን ዝቅተኛውን (Minimum)
የትምህርት ዝግጅት፣ የትምህርት ደረጃ እና የሥራ ልምድ አሟልቶ
መገኘት ይኖርበታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም ለአንድ ጊዜ
ምደባ ብቻ ተቀራራቢና ተዛማጅ የስራ ልምድ እና ዝቅተኛ
የትምህርት ዝግጅት አሟልተው የተገኙ ሠራተኞች ይወዳደራሉ፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተደነገገው ቢኖርም
በሠራተኞች ድልድል ጊዜ የሥራ መደቡን ዝቅተኛ ተፈላጊ
ችሎታ አሟልቶ የሚመደብ ሠራተኛ ካልተገኘ ብቻ ዝቅተኛ
የአገልግሎት ዘመኑን ለማሟላት 1 ዓመት እና ከዚያ በታች
የቀረው ሠራተኛ በታሳቢ ተመድቦ ለሥራ ደረጃው
ከተወሰነው ደመወዝ አንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ ይመደባል፡፡
ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን እንዳሟላም የሥራ ደረጃውን
ደመወዝ ያለውድድር ያገኛል፡፡
የተለያዩ ፆታ ያላቸው ሠራተኞች ለአንድ የሥራ መደብ
ተወዳድረው እኩል ነጥብ ካገኙ ለሴቷ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
እኩል ነጥብ ያመጡ ተወዳዳሪዎች ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው
ከሆኑ ከፍያለ የትምህርት ደረጃ ላለው ተወዳዳሪ ቅድሚያ
ይሰጣል ይህም ሆኖ እኩል ከመጡ በአገልግሎት ዘመን
ብልጫ ላለው ሠራተኛ ቅድሚያ ይሰጣል ይህም ሆኖ እኩል
ከወጡ አሸናፊው በእጣ ይለያል፣
5. ለማኀደር ጥራት የሚሰጥ ውጤት የሚያዘው ከሐምሌ
1/2001 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ መመሪያ የደልዳይ ኮሚቴው
ሥራ እስከጀመረበት ዕለት ድረስ በተወሰደ የዲስኘሊን
ግድፈት እርምጃ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
4.
6. በዚህ የሠራተኞች ድልድል የማይመደቡ ሠራተኞች
በባለስልጣኑ የሠራተኞች አስተዳደር ደንብ መሰረት
ይስተናገዳሉ፡፡
7. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 ድንጋጌ ተፈጻሚ እስኪሆን
ድረስ ምደባ ያላገኙ ሠራተኞች እስከ ሠራተኞች ድልድል
ጊዜ ይከፈላቸው የነበረውን ደመወዝ እንዲያገኙ
ይደረጋል፡፡
8. የመጀመሪያ ዲግሪ እና በላይ ለሚጠይቁ የስራ መደቦች
12ኛ ክፍልና አቻ ከመጠናቀቁ በፊት የተገኘ የስራ ልምድ
እንደ ስራ ልምድ አይያዝም፡፡
9.በክልል ደረጃ ከደረጀ 8 እስከ ደረጃ 12 ባሉ የሥራ
መደቦች የሥራ ምደባ የሚሰጣቸው የመጀመሪያ ዲግሪ አና
በላይ ያላቸው ሠራተኞች ብቻ መሆኑ ይታወቅ ፡፡
10.በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተደነገገው ቢኖርም የክልሉን
የግብር መንጀል መርማሪን አይመለከትም፡፡
11. ማንኛውም ሠራተኛ በዚህ የሠራተኞች ድልደል መመሪያ አንቀጽ
አምስት መሰረት በሠራተኞች የጽልደል መስፈርቶችና በተሰጣቸው
አንጻራዊ ክብደት ተመዝኖ ከ50% በታች ካገኘ ከሠራተኛ ድልድሉ
ውጭ ይሆናል/ወይም የስራ ምደባ አይሰጠውም፡፡
12. አንድ ሠራተኛ አሁን የሚከፈለው ደመወዝ ከተመደበበት የሥራ
መደብ መነሻ ደመወዝ ከፍ ያለ ከሆነ የያዘው ደመወዝ ብቻ
ይከፈለዋል፡፡
13. በዚህ የሠራተኞች ድልድል መመሪያ መሰረት በየደረጃው
በሚገኙ የገቢ ጽ/ቤቶች የመ/ቤቱ ሠራተኞች ድልድል
ከተጠናቀቀ በኋላ በሠራተኞች ያልተሸፈኑ ክፍት የሥራ
መደቦች በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች መ/ቤቶች በሥነምግባራቸውና በሙያ ብቃታቸው በሶስተኛ ወገን
በተመሰከረላቸው ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን በሚያሟሉ
ሠራተኞች ክፍት የስራ መደቡ በቀጥታ ምደባ እንዲሟላ
ይደረጋል፡፡
14.በተለያየ ምክንያት ከኃላፊነት የሚነሱ የጽ/ቤት ኃላፊዎች
ካላቸው የትም/ዝግጅትና የስራ ልምድ ጋር አግባብ ባለው
የስራ ሂደትና የስራ መደብ ተወዳድረው ይመደባሉ፣
15.በተለያየ ምክንያት ከኃላፊነታቸው የሚነሱ የስራ ሂደት
ባለቤቶች እና አስተባባሪዎች በስራ ላይ ባሉበት የስራ ሂደት
ተወዳድረው ይመደባሉ፣
16.በ3ቱ ከተሞች/ ባህር ዳር፣ ጐንደር እና ደሴ/ የተደራጁ
ወይም የሚደራጁ የቀበሌ የታክስ ማዕከላት ሠራተኞች
ድልድል በከተማ አስተዳደሩ የገቢ ጽ/ቤት ይፈጸማል፣
ክፍል አምስት
ሥለ ቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት
7. የቅሬታ አቀራረብ ሥነ - ሥርዓት
1. በድልደላው ላይ ቅሬታ የተሰማቸው ሠራተኛ
ቅሬታቸውን ምደባቸውን ካወቁበት ዕለት ጀምሮ ባሉት በ 2
ተከታታይ የሥራ ቀናት ለቅሬታ ሰሚ ቡድን ከነምክንያታቸው
ያቀርባሉ፡፡
2. የቅሬታ ሰሚ ቡድኑ ከቀረቡት ቅሬታዎች ውስጥ
መሠረታዊ ችግር የሌለባቸውንና በቀላሉ ሊፈቱ
የሚችሉትን ስህተቶች ከሰው ሀብት ስራ አመራር ጋር ተወያይቶ በ 2
ቀናት ጊዜ ውስጥ ይፈታል፡፡
3. በሠራተኞች የቀረበ ቅሬታ ከሰው ሀብት ስራ አመራር ጋር
የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን በዝርዝር አጣርቶ የደረሰበትን የውሣኔ
ሃሣብ በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ ለዋና ዳየሬክተሩ ወይም ውክልና
ለተሰጠው ኃላፊ ያቀርባል፡፡
4. ዋና ዳይሬክተሩ ወይም ውክልና የተሰጠው ኃላፊ የቀረበለትን
የውሣኔ ሃሣብ መርምሮ በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሣኔውን
ለቅሬታ ሰሚ ቡድን ያስተላልፋል፡፡
5. በሠራተኛ ድልድሉ ያልተስማማ ማንኛውም ሠራተኛ ቅሬታውን
በክልሉ መንግሰት የአገልግሎት አሰጣጥ ማስተግበሪያና የቅሬታ
ማስተናገጃ መመሪያ ደንብ ቁጥር 55/2000 መሰረት ሊያቀርብ
ይችላል፡፡
ክፍል ስድስት
በድልደላ የማይታቀፉ ሠራተኞች ስለሚሰተናገዱበት ሁኔታ
8. በሠራኛ ድልድሉ ስለማይታቀፉ ሠራተኞች
በባለስልጣኑ ከክልል እስከ ቀበሌ አስተዳደር እርከን ድረስ በሚገኙ
የገቢ ጽ/ቤቶች ባሉ የሥራ ሂደቶች ውስጥ ምደባ ያላገኙ ሠራተኞች
ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ በማይገቡበት፣ የክልሉ ሀብት ሊሸከመው
በሚችለው መጠንና በባለስልጣኑ የሠራተኞች አስተዳደር ደንብ
መሠረት ህይወታቸውን የሚመሩበት ሥርዓት መመቻቸት አለበት፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ የሚከተሉት አማራጮች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
1. የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመተግበርና በለውጡ ውስጥ
ለመስራት ብቃት ያላቸው ሠራተኞች በቅድሚያ በየደረጃው
በሚገኙ ገቢ ጽ/ቤቶች ውስጥ ባሉ ክፍት የሥራ መደቦች
እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም ወደ ለሎች
የገቢ ጽ/ቤቶች ተዛውረው መመደብ የማይፈልጉ እና ቦታ
ያልተገኘላቸው ሠራተኞች በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሌሎች
መ/ቤቶች ተመድበው እንዲሰሩ ባለስልጣኑ ከክልሉ ሲቪል
ሰርቪስ ቢሮ ጋር በመሆን የሚመደቡበትን ሁኔታ
ይመቻቻል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 በተደነገገው መሠረት
ተጠቃሚ ለመሆን ያልቻሉና እንዲሁም ከአገልግሎታቸውና
ከዕድሜያቸው አኳያና በሌሎች መመዘኛዎች በሌላ መ/ቤት
ተመድበው ለማገለገል ብቁና ውጤታማ የማይሆኑ ሠራተኞች
በመንግስት የማኀበራዊ የጡረታ ዋስትና ህግ መሰረት የጡረታ
መብታቸው እንዲከበር ይደረጋል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 3 በተደነገገው
የማይስተናገዱ ሠራተኞች በባለስልጣኑ የሠራተኞች
አስተዳደር ደንብ መሠረት የሚገባቸው ጥቅም ወይም የካሣ
ክፍያ ተሰጥቷቸው ይሰናበታሉ፡፡
5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 4 የተደነገገው ተፈጻሚ
እስኪሆን ድረስ በድልደላው ያልታቀፈ ሠራተኛ ቀደም ሲል
ሲከፈለው የነበረውን ወርሃዊ ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
6. በኮንትራት ቅጥር ላይ ያሉ ሠራተኞች የሥራ መደባቸው
በድልደላ ጊዜ በሠራተኛ ከተያዘ የሥራ ውሉ እንዲቋረጥ
ይደረጋል፡፡
ክፍል ሰባት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
9. የመመሪያው ተፈጻሚነት
ይህ መመሪያ ተፈጻሚ የሚሆነው በባለስልጣኑ አዲስ የአደረጃጀት
መዋቅር መሰረት ለአንድ ጊዜ ብቻ የተቋሙን ሠራተኞችን ለመደልደልና
የሥራ ደረጃና የመደብ መታወቂያ ቁጥር ለመስጠት ይሆናል፡፡
10. ህግ ተጠያቂነት
በዚህ የሠራተኛ ድልደላ ማስፈጸሚያ መመሪያ ከተፈቀደው ውጭ
ለማይገባው ሠራተኛ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም አሳልፎ የሰጠ አካል አግባብ
ባለው ሕግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
11. ስለተሻሩና ተፈጻሚነት ሰለማይኖራቸው ህጐች
1. ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሌላ
መመሪያ ወይም የተለመደ አሰራር በዚህ
መመሪያ ውስጥ በተሸፈኑት ጉዳዩች ላይ
ተፈጻሚነት አይኖረውም፣
2. በዚህ መመሪያ መሰረት የሠራተኛ ድልደላ
ከተካሄደ በኋላ የትምህርት ደረጃችንን
አሻሽለናል በማለት የትምህርት ደረጀ መነሻ
ደመወዝ የሚጠይቁ ቢኖሩ አይስተናገዱም፡፡
12. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
1. ይህ መመሪያ ከጥር 1 ቀን 2003 ቀን ጀምሮ
የፀና ይሆናል፣
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሰረት
በድልደላ መመሪያው መሰረት የተመደቡ ሠራተኞች እና
ተሚዎች ለየሥራ ደረጃው የተወሰነውን መነሻ ደመወዝና
ጥቅማጥቅም የሚያገኙት ከጥር 1 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ
ይሆናል፡፡
አመሰግናለሁ
10 Q
53